- Main
- Catalog
- News and Media
- 𝗔𝗕𝗖 𝗡𝗘𝗪𝗦 𝗔𝗠𝗛𝗔𝗥𝗜𝗖
𝗔𝗕𝗖 𝗡𝗘𝗪𝗦 𝗔𝗠𝗛𝗔𝗥𝗜𝗖
This public channel features all aspects of life in # Ethiopia, # News # Zena # News #Reviews
Channel statistics
የኢራን ጦር፥ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የባህር ላይ እገዳ ከቀጠለ ፦
- በቀይ ባህር
- በፋርስ ባህረ ሰላጤ
- በኦማን ባህር ላይ የሚደረጉ ማናቸውንም የንግድ እንቅስቃሴዎችን ሙሉ ለሙሉ እንደሚያግድ አስጠንቅቋል።
የኢራን ወታደራዊ ማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ አሊ አብዶላሂ እንደተናገሩት አሜሪካ በኢራን የንግድ እና የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ የምታደርገውን ወከባና እገዳ ካላቆመች የኢራን ጦር ማናቸውም ምርቶች ወደ ቀጣናው እንዳይገቡም ሆነ እንዳይወጡ ያደርጋል።
ኢራን የአሜሪካን እርምጃ በቅርቡ የተደረሰውን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ለመጣስ እንደ " ቅድመ ሁኔታ " እንደምትቆጥረው ገልጻለች።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሰኞ ባስተላለፉት ትዕዛዝ የአሜሪካ ባህር ኃይል ወደ ኢራን የሚገቡና የሚወጡ ማናቸውንም መርከቦች እንዳይሳለጡ እገዳ ጥሏል።
እስካሁን ባለው መረጃ የአሜሪካ ባህር ኃይል ቢያንስ 8 ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸውን የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ጉዟቸውን እንዲያቋርጡ አድርጓል።
አሁን በሆርሙዝ ሰርጥ ያለው እንቅስቃሴ በመስተጓጎሉ የዓለም ነዳጅ ዋጋ የጨመረ ሲሆን የበርካታ ሀገራት ኢኮኖሚ ተናግቷል።
ኢራን እንደዛተችው በቀይ ባህርና ሌሎች መስመሮች እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ የምታደርግ ከሆነ ቀውሱ በተለያዩ ሀገራት ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።
በሌላ በኩል፤ ትራምፕ በቀጣይ ሁለት ቀናት ከኢራን ጋር ሁለተኛ ዙር ድርድር እንደሚጀመር ፍንጭ ሰጥተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 7 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲወርድ ለማድረግ ፓኪስታን ሁለተኛ ዙር ድርድር እንዲደረግ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ታውቋል።
በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄ.ዲ. ቫንስ የመጀመሪያው ድርድር ያለ ስምምነት ሊበተን ስለቻለበት ምክንያት ለፎክስ ኒውስ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቫንስ እንደገለጹት፣ አሜሪካ ከንግግሩ የወጣችው ኢራን ከአሜሪካ የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ ስላደረገች ሳይሆን በድርድር ክፍሉ ውስጥ የነበሩት የኢራን ተደራዳሪዎች " ውሳኔ የመስጠት ስልጣን (Authorization) " ስለሌላቸው ነው።
" እንደ ጋሊባፍ እና አራቅቺ ያሉ ባለስልጣናት ስምምነት ላይ ለመድረስ ፍላጎት ቢኖራቸውም የመጨረሻውን ቃል የሚናገሩት አካላት ግን አልፈቀዱላቸውም " ብለዋል።
እውነተኛዎቹ ውሳኔ ሰጪዎች የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) እና በአሁኑ ወቅት በህክምና ላይ ናቸው ተብለው የሚገመቱት አዲሱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ሞጅታባ ኻሜኒ እንደሆኑ ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን ስምምነት ባይደረስም ቫንስ በኢስላማባድ ያሳለፉትን 21 ሰዓታት " ጠቃሚ " ብለዋቸዋል።
አሜሪካ በዚህ ሂደት ውስጥ፥ ኢራን እንዴት እንደምትደራደር እና ትክክለኛው የሥልጣን ቁልፍ በማን እጅ እንደሆነ ጠቃሚ መረጃ ማግኘቷን ገልጸዋል።
በዲፕሎማሲው ቋንቋ " ብዕሩን የጨበጠው ማን እንደሆነ አውቀናል " ብለዋል። ይህ ማለት ወደፊት ከማን ጋር መነጋገር እንዳለባቸው ግልጽ ሆኖላቸዋል።
አሜሪካ " ስምምነት " ላይ ለመድረስ አሁንም በሩ ክፍት እንደሆነ ብታምንም ግን የማይደራደሩ ነጥቦች እንዳሉ አረጋግጣለች።
እነዚህም ፦
- የሆርሙዝ ሰርጥ ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆኖ ለንግድ ዝውውር ምቹ መሆን አለበት።
- ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ለኒውኩሌር መሳሪያ እንዳይውል ማድረግ። የኒውኩሌር ባለቤት እንዳትሆን።
... የሚሉት ናቸው።
ቫንስ " አሁንም ኳሱ በኢራን እጅ ነው " ብለዋል።
አሁን ፓኪስታን ሁለተኛው ዙር ድርድር ተካሂዶ በሁለቱም ወገን አስተማማኝ ስምምነት ተደርሶ የዓለም ህዝብ እፎይ እንዲል ጥረት እያደረገች ነው።
በሌላ የመካከለኛው ምስራቅ ዜና ፥ የእስራኤል እና የሊባኖስ አምባሳደሮች ልዩ የተባለ የሰላም ንግግር በዛሬው ዕለት በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ውስጥ ያደርጋሉ።
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሌላቸው የእስራኤል እና ሊባኖስ ባለሥልጣናት ለቀጥታ ንግግር ፊት ለፊት ሲገናኙ በአስርት ዓመታት ውስጥ ይህ የመጀመሪያው ነው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ልዩ በሆነው የቀጥታ ንግግር እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
የሊባኖስ ሹማምንት በመጀመሪያ እስራኤል ሄዝቦላህ ላይ የከፈተችው ጦርነት ላይ የተኩስ አቁም እንዲደረስ የማስማማት ፍላጎት አላቸው።
እስራኤል መጀመሪያ በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ ቡድን " ትጥቁን ይፍታ " ባይ ናት።
ሄዝቦላህ በበኩሉ የሁለቱ አገራትን ንግግር ውድቅ በማድረግ ስምምነት ለሚደረስበት ማንኛውም ጉዳይ እንደማይገዛ አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፎክስ ኒውስ እንዲሁም ከቢቢሲ ነው ያገኘው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ/ም

በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዘርፍ ዛሬም ድረስ ስሙ በጉልህ የሚነሳውና በርካታ አድናቂዎች ያሉት አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከ9 ዓመታት በኋላ አዲስ አልበም ነገ ለአድማጮቹ ያቀርባል።
አርቲስቱ " ኢትዮጵያ " የተሰኘውን አልበሙን የዛሬ 9 ዓመት ለአድማጩ ካደረሰ በኋላ ነገ " ኢትዮሪካ " የተሰኝ አልበሙን በራሱ የዩትዩብ ቻናል ላይ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ማዳመጫ ድረገጾች ላይ እንደሚለቅ ተገልጿል።
አልበሙ ምንም እንኳን " ሰዋሰው መልቲሚዲያ " በተሰኘው የዘፈን አቅራቢ ድርጅት በኩል ለህዝብ ይደርሳል ተብሎ ቢነገርም በመካከል አለመግባባት ተፈጥሮ በራሱ መንገድ ወደ አድማጭ እንደሚያደርሰው ነው የተሰማው።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህን አለመግባባት አጀንዳ ያደረጉና ያራገቡ የተለያዩ ገጾች ጉዳዩን ቀጥታ ከፖለቲካ ጋር እንደሚያያዝ ሲገልጹና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ከርመዋል።
ስምምነቱ የፈረሰው ለምድነው ?
እንደ " ኢትዮፒካሊንክ " የመዝናኛና መረጃ የሬድዮ ፕሮግራም ከሆነ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር የነበረውን ውል በስምምነት ነው ያፈረሰው።
ስምምነቱ የፈረሰው በአሳታሚውና በአርቲስቱ በኩል ውል ውስጥ የተካተቱት አዳዲስ ጉዳዮች ልዩነት ለመፍጠራቸው ነው።
ሁለቱ አካላት ከአራት አመት በፊት ነው ስምምነት የተፈራረሙት። ውሉን ለማደስ በነበረ ሂደት ግን አዳዲስ ሃሳቦች በመግባታቸው አለመግባባቶች ተፈጥረዋል።
ሰዋሰው በአዲሱ ውል ላይ ቀደም ያሉ የቴዴ አፍሮ ዘፈኖችን በሰዋሰው መተግበሪያ ላይ እንዲጫኑና ለዚህም በየአመቱ የሚከፈል ገንዘብ በቅድመ ክፍያ ለመክፈል ፍላጎቱን ገልጿል።
ይህ ሃሳብ ግን በቴዲ በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
በተጨማሪ ከአራት ዓመት በፊት በተፈረመው ውል ላይ ከስልክ ድምጽ ማሳመሪካ CRBT የሚገኝ ገቢ ለሰዋሰው እንዲሰጥ የሚፈቅደውን ስምምነት ማሻሻያ እንዲደረግበት በቴዲ የቀረበው ጥያቄ ከሰዋሰው ይሁንታ አላገኘም።
ልዩነቶቹ ሊጠቡ ባለመቻላቸውና የአልበሙ መውጫ በመድረሱ ሁለቱም ወገኖች ውሉን በስምምነት አቋርጠዋል።
ውሉ ሲፈረም ሰዋሰው ለቴዲ አጠቃላይ 50 ሚሊዮን ብር ለመክፈል ተስማምቶ ነበር። የዚህንም ግማሽ 25 ሚሊዮን ብር በወቅቱ ተከፍሎት ነበር።
አልበሙ እንዲወጣ ስምምነት ላይ ተደርሶ የነበረው ከአራት አመት በፊት የነበረ ቢሆንም በተለያዩ አለመግባባቶች ምክንያት ውሉ ሊታደስ አልቻለም። በመጨረሻም ውሉ በሰላማዊ መግባባት ፈርሷል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ቴዲና አሳታሚው ድርጅት ውይይት አድርገው ውሉን ለማደስ ባለመግቤታችው ቴዲ ወስዶት የነበረውን 25 ሚሊዮን ብር ከአራት አመት የባንክ ወለድ ጋር ታሳቢ ተደርጎ 33 ሚሊዮን ብር ለሰዋሰው መመለሱን የአርቲስቱ የማናጅመንት ባልደረባ ተናግረዋል።
ሰዋሰው መልቲሚዲያም አርቲስቱ የወሰደውን ግማሽ ክፍያ 25 ሚሊዮን ብር ከአራት አመት የባንክ ወለድ ጋር ጨምሮ መመለሱን አረጋግጧል።
አሳታሚው " በስራ ሂደት በሚያጋጥሙ ሃሳቦች ምክንያት ውሉ በስምምነት ነው የተፈረሰው " ብሏል።
ቴዲ አፍሮ " ኢትዮሪካ " የተሰኘው አልበሙን ነገ ሀሙስ ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በራሱ ዩትዩብ ቻናል እንዲሁም በተለያዩ የማዳመጫ አማራጮች ለህዝብ ያደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
አልበሙ ቅዳሜ ይወጣል ቢባልም ቀደም ብሎ እንዲወጣ የተወሰነው በቴዲ አፍሮ መሆኑን እንዲሁም የወር ፣ የቀን እና ሰዓቱ ቁጥር ግጥምጥሞሽ አርቲስቱ በምክንያት ያደረገው መሆኑን የማናጅመንት ክፍሉ ለ" ኢትዮፒካሊንክ " የመዝናኛና መረጃ ፕሮግራም አሳውቋል።
NB. ስምምነቱ ሊፈርስ ስለቻለበት ምክንያት እና አርቲስቱ ስለመለሰው የገንዘብ መጠን ሙሉ መረጃው የተወሰደው ከ " ኢትዮፒካሊንክ " የሬድዮ ፕሮግራም ነው።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ሄደው የነበረው ከደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር በመመካከርና በመስማማት እንደሆነ አሳወቁ።
ፌዴራል መንግሥት ለአንድ ዓመት ስልጣናቸውን ያራዘመላቸው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ወደ አዲስ አበባ ያደረጉት ጉዞ የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በሚያውቁትና በመከሩበት እንዲሁም በተስማሙበት መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳብራሩት በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙት በፌደራል መንግስት በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ሲሆን ጉዞውም የፕሪቶሪያ ውል ፈራሚ ከሆነው ህወሓት ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በመመካከርና በመስማማት የተደረገ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ በአዲስ አበባ ለፌደራል መንግስት ያቀረቡት ሪፖርት የክልሉ መሥሪያ ቤቶች የሥራ አፈጻጸምን መሠረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
" በሪፖርቱና በውይይቱ ከተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፦
- ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስና የትግራይ ክልልን ግዛት እንዲከበር ማድረግ፣
- በጦርነት የወደሙ ተቋማትን መልሶ መገንባት፣
- በትምህርትና ጤና ዘርፍ ያሉ እንቅስቃሴዎች፣
- የበጀት መቋረጥን ተከትሎ የተከሰተው የመድኃኒት እጥረት ይገኙበታል " ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ከጦርነቱ በኋላ የክልሉ የእርሻ እንቅስቃሴ መልሶ ለማነቃቃት ሊገቡ ከተፈቀዱት 500 ትራክተሮች 85 ከገቡ በኋላ ጅቡቲ ወደብ የቀሩበት ምክንያት በሪፓርቱ ለፌደራል መንግስት በጥያቄ መልክ መቅረቡን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፥ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ህወሓት ወጥቶ ስለተቃወመው የስልጣን ዘመናቸው ለአንድ አመት መራዘም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
" መጋቢት 30/2018 ዓ.ም ይጠናቀቅ የነበረው የጊዚያዊ አስተዳደሩ የስልጣን ጊዜ ተከትሎ የስልጣን ክፍተት ተከስቶ ክልሉ መንግስት አልባ እንዳይሆን ከሁለት ወር በፊት ጀምሮ ከፌደራል መንግስት ምክክር ሲደረግበት ነበር " ብለዋል።
" ወደ አዲስ አበባ ስጓዝ የፕሪቶሪያ ውል ፈራሚ ከሆነው ህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በመመካካርና በመስማማት ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የስልጣን ዘመን በአንድ አመት መራዘሙ ይፋ ከተደረገ በኋላ ህወሓት " የተናጠል " ውሳኔ ነው በሚል በመግለጫ እንደተቃወመው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ሄደው የነበረው ከደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር በመመካከርና በመስማማት እንደሆነ አሳወቁ።
ፌዴራል መንግሥት ለአንድ ዓመት ስልጣናቸውን ያራዘመላቸው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ወደ አዲስ አበባ ያደረጉት ጉዞ የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በሚያውቁትና በመከሩበት እንዲሁም በተስማሙበት መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳብራሩት በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙት በፌደራል መንግስት በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ሲሆን ጉዞውም የፕሪቶሪያ ውል ፈራሚ ከሆነው ህወሓት ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በመመካከርና በመስማማት የተደረገ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ በአዲስ አበባ ለፌደራል መንግስት ያቀረቡት ሪፖርት የክልሉ መሥሪያ ቤቶች የሥራ አፈጻጸምን መሠረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
" በሪፖርቱና በውይይቱ ከተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፦
- ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስና የትግራይ ክልልን ግዛት እንዲከበር ማድረግ፣
- በጦርነት የወደሙ ተቋማትን መልሶ መገንባት፣
- በትምህርትና ጤና ዘርፍ ያሉ እንቅስቃሴዎች፣
- የበጀት መቋረጥን ተከትሎ የተከሰተው የመድኃኒት እጥረት ይገኙበታል " ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ከጦርነቱ በኋላ የክልሉ የእርሻ እንቅስቃሴ መልሶ ለማነቃቃት ሊገቡ ከተፈቀዱት 500 ትራክተሮች 85 ከገቡ በኋላ ጅቡቲ ወደብ የቀሩበት ምክንያት በሪፓርቱ ለፌደራል መንግስት በጥያቄ መልክ መቅረቡን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፥ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ህወሓት ወጥቶ ስለተቃወመው የስልጣን ዘመናቸው ለአንድ አመት መራዘም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
" መጋቢት 30/2018 ዓ.ም ይጠናቀቅ የነበረው የጊዚያዊ አስተዳደሩ የስልጣን ጊዜ ተከትሎ የስልጣን ክፍተት ተከስቶ ክልሉ መንግስት አልባ እንዳይሆን ከሁለት ወር በፊት ጀምሮ ከፌደራል መንግስት ምክክር ሲደረግበት ነበር " ብለዋል።
" ወደ አዲስ አበባ ስጓዝ የፕሪቶሪያ ውል ፈራሚ ከሆነው ህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በመመካካርና በመስማማት ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የስልጣን ዘመን በአንድ አመት መራዘሙ ይፋ ከተደረገ በኋላ ህወሓት " የተናጠል " ውሳኔ ነው በሚል በመግለጫ እንደተቃወመው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲወርድ ለማድረግ ፓኪስታን ሁለተኛ ዙር ድርድር እንዲደረግ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ታውቋል።
በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄ.ዲ. ቫንስ የመጀመሪያው ድርድር ያለ ስምምነት ሊበተን ስለቻለበት ምክንያት ለፎክስ ኒውስ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቫንስ እንደገለጹት፣ አሜሪካ ከንግግሩ የወጣችው ኢራን ከአሜሪካ የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ ስላደረገች ሳይሆን በድርድር ክፍሉ ውስጥ የነበሩት የኢራን ተደራዳሪዎች " ውሳኔ የመስጠት ስልጣን (Authorization) " ስለሌላቸው ነው።
" እንደ ጋሊባፍ እና አራቅቺ ያሉ ባለስልጣናት ስምምነት ላይ ለመድረስ ፍላጎት ቢኖራቸውም የመጨረሻውን ቃል የሚናገሩት አካላት ግን አልፈቀዱላቸውም " ብለዋል።
እውነተኛዎቹ ውሳኔ ሰጪዎች የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) እና በአሁኑ ወቅት በህክምና ላይ ናቸው ተብለው የሚገመቱት አዲሱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ሞጅታባ ኻሜኒ እንደሆኑ ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን ስምምነት ባይደረስም ቫንስ በኢስላማባድ ያሳለፉትን 21 ሰዓታት " ጠቃሚ " ብለዋቸዋል።
አሜሪካ በዚህ ሂደት ውስጥ፥ ኢራን እንዴት እንደምትደራደር እና ትክክለኛው የሥልጣን ቁልፍ በማን እጅ እንደሆነ ጠቃሚ መረጃ ማግኘቷን ገልጸዋል።
በዲፕሎማሲው ቋንቋ " ብዕሩን የጨበጠው ማን እንደሆነ አውቀናል " ብለዋል። ይህ ማለት ወደፊት ከማን ጋር መነጋገር እንዳለባቸው ግልጽ ሆኖላቸዋል።
አሜሪካ " ስምምነት " ላይ ለመድረስ አሁንም በሩ ክፍት እንደሆነ ብታምንም ግን የማይደራደሩ ነጥቦች እንዳሉ አረጋግጣለች።
እነዚህም ፦
- የሆርሙዝ ሰርጥ ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆኖ ለንግድ ዝውውር ምቹ መሆን አለበት።
- ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ለኒውኩሌር መሳሪያ እንዳይውል ማድረግ። የኒውኩሌር ባለቤት እንዳትሆን።
... የሚሉት ናቸው።
ቫንስ " አሁንም ኳሱ በኢራን እጅ ነው " ብለዋል።
አሁን ፓኪስታን ሁለተኛው ዙር ድርድር ተካሂዶ በሁለቱም ወገን አስተማማኝ ስምምነት ተደርሶ የዓለም ህዝብ እፎይ እንዲል ጥረት እያደረገች ነው።
በሌላ የመካከለኛው ምስራቅ ዜና ፥ የእስራኤል እና የሊባኖስ አምባሳደሮች ልዩ የተባለ የሰላም ንግግር በዛሬው ዕለት በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ውስጥ ያደርጋሉ።
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሌላቸው የእስራኤል እና ሊባኖስ ባለሥልጣናት ለቀጥታ ንግግር ፊት ለፊት ሲገናኙ በአስርት ዓመታት ውስጥ ይህ የመጀመሪያው ነው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ልዩ በሆነው የቀጥታ ንግግር እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
የሊባኖስ ሹማምንት በመጀመሪያ እስራኤል ሄዝቦላህ ላይ የከፈተችው ጦርነት ላይ የተኩስ አቁም እንዲደረስ የማስማማት ፍላጎት አላቸው።
እስራኤል መጀመሪያ በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ ቡድን " ትጥቁን ይፍታ " ባይ ናት።
ሄዝቦላህ በበኩሉ የሁለቱ አገራትን ንግግር ውድቅ በማድረግ ስምምነት ለሚደረስበት ማንኛውም ጉዳይ እንደማይገዛ አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፎክስ ኒውስ እንዲሁም ከቢቢሲ ነው ያገኘው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲወርድ ለማድረግ ፓኪስታን ሁለተኛ ዙር ድርድር እንዲደረግ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ታውቋል።
በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄ.ዲ. ቫንስ የመጀመሪያው ድርድር ያለ ስምምነት ሊበተን ስለቻለበት ምክንያት ለፎክስ ኒውስ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቫንስ እንደገለጹት፣ አሜሪካ ከንግግሩ የወጣችው ኢራን ከአሜሪካ የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ ስላደረገች ሳይሆን በድርድር ክፍሉ ውስጥ የነበሩት የኢራን ተደራዳሪዎች " ውሳኔ የመስጠት ስልጣን (Authorization) " ስለሌላቸው ነው።
" እንደ ጋሊባፍ እና አራቅቺ ያሉ ባለስልጣናት ስምምነት ላይ ለመድረስ ፍላጎት ቢኖራቸውም የመጨረሻውን ቃል የሚናገሩት አካላት ግን አልፈቀዱላቸውም " ብለዋል።
እውነተኛዎቹ ውሳኔ ሰጪዎች የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) እና በአሁኑ ወቅት በህክምና ላይ ናቸው ተብለው የሚገመቱት አዲሱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ሞጅታባ ኻሜኒ እንደሆኑ ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን ስምምነት ባይደረስም ቫንስ በኢስላማባድ ያሳለፉትን 21 ሰዓታት " ጠቃሚ " ብለዋቸዋል።
አሜሪካ በዚህ ሂደት ውስጥ፥ ኢራን እንዴት እንደምትደራደር እና ትክክለኛው የሥልጣን ቁልፍ በማን እጅ እንደሆነ ጠቃሚ መረጃ ማግኘቷን ገልጸዋል።
በዲፕሎማሲው ቋንቋ " ብዕሩን የጨበጠው ማን እንደሆነ አውቀናል " ብለዋል። ይህ ማለት ወደፊት ከማን ጋር መነጋገር እንዳለባቸው ግልጽ ሆኖላቸዋል።
አሜሪካ " ስምምነት " ላይ ለመድረስ አሁንም በሩ ክፍት እንደሆነ ብታምንም ግን የማይደራደሩ ነጥቦች እንዳሉ አረጋግጣለች።
እነዚህም ፦
- የሆርሙዝ ሰርጥ ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆኖ ለንግድ ዝውውር ምቹ መሆን አለበት።
- ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ለኒውኩሌር መሳሪያ እንዳይውል ማድረግ። የኒውኩሌር ባለቤት እንዳትሆን።
... የሚሉት ናቸው።
ቫንስ " አሁንም ኳሱ በኢራን እጅ ነው " ብለዋል።
አሁን ፓኪስታን ሁለተኛው ዙር ድርድር ተካሂዶ በሁለቱም ወገን አስተማማኝ ስምምነት ተደርሶ የዓለም ህዝብ እፎይ እንዲል ጥረት እያደረገች ነው።
በሌላ የመካከለኛው ምስራቅ ዜና ፥ የእስራኤል እና የሊባኖስ አምባሳደሮች ልዩ የተባለ የሰላም ንግግር በዛሬው ዕለት በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ውስጥ ያደርጋሉ።
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሌላቸው የእስራኤል እና ሊባኖስ ባለሥልጣናት ለቀጥታ ንግግር ፊት ለፊት ሲገናኙ በአስርት ዓመታት ውስጥ ይህ የመጀመሪያው ነው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ልዩ በሆነው የቀጥታ ንግግር እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
የሊባኖስ ሹማምንት በመጀመሪያ እስራኤል ሄዝቦላህ ላይ የከፈተችው ጦርነት ላይ የተኩስ አቁም እንዲደረስ የማስማማት ፍላጎት አላቸው።
እስራኤል መጀመሪያ በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ ቡድን " ትጥቁን ይፍታ " ባይ ናት።
ሄዝቦላህ በበኩሉ የሁለቱ አገራትን ንግግር ውድቅ በማድረግ ስምምነት ለሚደረስበት ማንኛውም ጉዳይ እንደማይገዛ አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፎክስ ኒውስ እንዲሁም ከቢቢሲ ነው ያገኘው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
በዓመት 8 ሺ ህፃናት በካንሰር በሽታ በሚጠቁባት ኢትዮጵያ ህክምና የሚሰጡ ሆስፒታሎች ብዛት በጣም አነስተኛ በመሆኑ መጨመር እንደሚገባ የኢትዮጵያ የህፃናት የደምና ካንሰር ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አቤል ኃይሉ በሰጡን ቃል፣ ያሉት ሆስፒታሎች ከስምንት እንደማይበልጡ ገልጸው፣ " በዓመት እስከ 8 ሺሕ ልጆች በካንሰር በሚታሙባት ኢትዮጵያ ያሉት 8 ሆስፒታሎች በቂ አይደሉም " ብለዋል።
ለህፃናት ካንሰር ህመም የህክምና አገልግሎት የሚሰጡት ሆስፒታሎች፥
° ነቀምት፣
° ጥቁር አንበሳ፣
° ጅማ፣
° ሀዋሳ፣
° ጎንደር፣
° መቐለ፣
° ባህርዳር፣
° አምቦ መሆናቸውን ገልጸው አገልግሎቱን ለማስፋፋት ማህበሩ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የዘርፉ ምሁራን እንደሚሉት በተለይ ህፃናት ከካንሰር ህመም የመዳን እድላቸው ከፍተኛ ነው። ዶ/ር አቤል በበኩላቸው፣ " በጥቁር አንበሳና እና በሌሎች ሆስፒታሎች ታክመው የዳኑ ብዙ ልጆች አሉን። ሥራ የያዙ፣ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያሉ በካንሰር ተጠቅተው የዳኑ ልጆች አሉ " ሲሉ መስክረዋል።
ለመዳን ደግሞ ህፃናቱ የኬሞቴሪፒ ቴራፒ ህክምና፣ የቀዶ ጥገና ህክምና፣ የጨረር ህክምና እንደሚያስፈልጋቸውም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" ለምሳሌ የኩላሊት፣ የጡንቻ ካንሰር ከሆነ በካንሰር የተጠቃው ኩላሊት በሰርጀሪ መውጣት ይኖርበታል " ያሉት ዶ/ር አቤል፣ " የጨረር ህክምና ሁሉም አይፈልግም፤ ያስፈልጋል ለሚባልባቸው የካንሰር አይነቶች ግን በጣም ፍቱን የሆነ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል " ብለዋል።
ከ15 እና ከ20% የማይልጥ ደግሞ ንቅለ ተከላ ህክምና እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ " የንቅለ ተከላ ህክምና ገና በኢትዮጵያ አልጀመርንም " በማለትም ተናግረዋል።
" ድጋፍ ሰጭ የሆነው የደም ህክምናም በጣም አስፈላጊ ነው፤ ሰዎች ደም ሊለግሱ ይገባል። ደም ከሌለ ከደም ካንሰር ጋር የተገኙትን ለማከም ያስቸግራል " ሲሉም ገልጸዋል።
በተያያዘ ገለጻ፣ የኬሞቴራፒ መድኃኒት፣ የጨረር ህክምና ሰርቪስ፣ የባለሙያዎች እጥረትም ዘርፉን በዋናነት እየፈተነው መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት ዶ/ር አቤል፣ ጤና ሚኒስቴር፣ በጤና ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ሚዲያዎች ከተረባረቡ ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻል ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል፥ በርካታ የካንሰር ህሙማን ውጭ ሀገር ሄደው የሚታከሙት ኢትዮጵያ ውስጥ ምን አይነት ህክምና ስለሚጎድል ነው? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ በዋናኝነት ምርመራ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ነገሮችና አንዳንድ እንደ ዘረመል ህክምናዎች ስለሌሉ መሆኑን አስረድተዋል።
ቲክቫህኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

በቅርብ ጊዜ የጓደኞቻችሁን ወይም የምታውቋቸው ሰዎች ስም የዋትስአፕ (WhatsApp) አካውንቶችን በመጥለፍ / Hack በማድረግ የገንዘብ ማጭበርበር ድርጊቶች በስፋት እየተፈጸሙ ይገኛሉ።
ማጭበርበሪያው እንዴት ነው እየተፈጸመ ያለው ?
አጭበርባሪዎቹ የቅርብ ጓደኛችሁን ወይም ደግሞ የምታውቁትን ሰው አካውንት ከተቆጣጠሩ በኋላ የእነሱን ምስል እና ስም በመጠቀም መልዕክት ይልኩላችኋል።
" የባንክ ትራንስፈር ሊሚት ስለሞላብኝ፣ ለአንድ ሰው አሁን 50,000 ብር (ወይም ሌላ መጠን) ላክልኝ፤ ነገ ጠዋት እመልስልሃለሁ " የሚል አስቸኳይ ጥያቄ ያቀርባሉ።
ብሩን የምትልኩበትን የማታውቁትን ሰው ስም እና የባንክ አካውንት ይልኩላችኋል።
እናተም " ጓደኛዬ ተቸገረ ፤ ነገ ይመልሳል " ብላችሁ ትልካለችሁ። ከዛም ሰውየው የውሃ ሽታ ሆኖ ይቀራል።
ለምሳሌ ከቀናት በፊት አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በዚህ መንገድ 50 ሺህ ብር ተጭበርብሯል።
ወንጀለኞች የሰዎችን አጣዳፊ ችግር እና መተማመን ለክፉ ዓላማቸው ስለሚጠቀሙበት ማንኛውንም የገንዘብ ዝውውር ከማድረጋችሁ በፊት ደውሎ ማረጋገጥ ብቸኛው አስተማማኝ መንገድ ነው።
ለጥንቃቄ ፦
1. በዋትስአፕ የገንዘብ ጥያቄ ሲቀርብላችሁ፣ መልዕክቱን የላከው ሰው ትክክለኛ ጓደኛችሁ መሆኑን ለማረጋገጥ በስልክ መስመር ደውላችሁ አነጋግሩት።
2. ወደ ስልካችሁ የሚመጣን ማንኛውንም የSMS የማረጋገጫ ኮድ ለማንም ሰው በፍጹም አትስጡ።
3. በዋትስአፕ ሴቲንግ ውስጥ በመግባት 'Two-Step Verification' ማብራታችሁን እርግጠኛ ሁኑ።
የዋትስአፕ አካውንታችን ይጠለፋል ?
አዎ ይጠለፋል ፤ ነገር ግን አጠላለፉ እንደ ኮምፒውተር ቫይረስ በቀጥታ ሲስተሙን ሰብሮ በመግባት ሳይሆን አብዛኛውን ጊዜ ተጠቃሚውን በማታለል የሚፈጸም ነው።
° የSMS ኮድ ማጭበርበር ፦ ይህ አሁን ላይ በብዛት ማጭበርበር እየተፈጸመበት ያለው መንገድ ነው። አጭበርባሪድ የእንተን ስልክ ቁጥር ተጠቅሞ ዋትስአፕ ለመክፈት ይሞክራል፤ ከዚያ ዋትስአፕ ለእናተ የማረጋገጫ ኮድ ይልካል። አጭበርባሪው በተለያየ ዘዴ ለምሳሌ ፦ " ኮዱ በስህተት አንተ ጋር ስለሄደ ንገረኝ " በማለት ያንን ኮድ ይቀበላችኋል። ኮዱን ካገኘ በኋላ የናተን ዋትስአፕ በራሱ ስልክ ላይ ይከፍተዋል።
° ዋትስአፕ ዌብ ፦ አንድ ሰው ስልካችሁን ለአፍታ አግኝቶ በዋትስአፕ ዌብ አማካኝነት የQR ኮዱን በራሱ ኮምፒውተር ወይም ስልክ ላይ ስካን ካደረገ አናተ የምትልኳቸውና የመጡላችሁ መልዕክቶች በሙሉ በቀጥታ ማየት ይችላል።
° ስፓይዌር ፦ ይህ እጅግ በጣም የላቀ ጠለፋ ነው። ስልካችሁ ላይ አደገኛ ሊንኮችን ስትነኩ ወይም ኦፊሴላዊ ያልሆኑ መተግበሪያዎችን እንደ እነ GB WhatsApp ስትጭኑ ስልኩ ውስጥ የሚቀመጥ ሰላይ ሶፍትዌር መልዕክቶችህን ለሌላ አካል ሊያስተላልፍ ይችላል።
እንዴት መከላከል ይቻላል ?
1. ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) ፦ ወደ Settings > Account > Two-Step Verification > Enable ማድረግ። የራስህን የ6 አሃዝ ሚስጥር ቁጥር (PIN) መፍጠር። ይህ ካለ አጭበርባሪው የSMS ኮዱን እንኳ ቢያገኝ ይህንን PIN ካላወቀ አካውንቱን ሊከፍተው አይችልም።
2. Linked Devices መፈተሽ ፦ ዘወትር Settings > Linked Devices የሚለውን በመጫን አናተ የማታውቁት ኮምፒውተር ወይም ስልክ መኖሩን አረጋግጡ። ካለ "Log Out" አድርጉት።
3. ኮድ ለማንም አትስጡ ፦ ማንኛውንም ዓይነት የ6 አሃዝ ቁጥር በSMS ሲመጣላችሁ ለሰው አትናገሩ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 3 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የምስራቅ ቀጠና ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ላይ በኃላፊነትና በባለሙያነት ሲያገለግሉ የነበሩት ፦
1. ሌ/ኮሎኔል ኢንጂነር አዲሱ ጎኣ (የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ)
2. አቶ ሳሙኤል ማሞ (የፕሮጀክቱ ሾፌር)
3. ኢንጂነር በረከት ኡታ (ከኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ አማካሪና ተቆጣጣሪ መሐንዲስ)
ባጋጠማቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተቋሙ በታላቅ ሀዘን አስታውቋል።
" እነዚህ ውድ የሥራ ባልደረቦች ተቋማዊና ሀገራዊ ግዳጃቸውን በላቀ ዲስፕሊንና በትጋት ሲወጡ የነበሩ፣ በሙያዊ ብቃታቸውና ለሥራ በነበራቸው ቁርጠኝነት ዘወትር የሚታወሱ ናቸው " ብሏል።
መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሟች ቤተሰቦች ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ መፅናናትንና ብርታትን ተመኝቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም
@tikvahethiopia
ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ ፦
" አሁን ላይ የካንሰር ታማሚ አይደለሁም ፤ የካንሰር ሰርቫይቨር ነኝ። ከካንሰር ሂደት ውስጥ እንዳለፈ ሰው የህይወት ተሞክሮ ላይ አጠር ያለ ቀለል ያለ ሁለት ነገሮችን ተምሪያለሁ፤ እንደ ህይወት መርህም ለመከተል እየተለማመድኳቸው ነው።
ስለ ትንንሽ ነገሮች ማመስገን ያስፈልጋል። ህይወት ስጦታ ነው። ስጦታ መሆኑን አምነን ደግሞ ማመስገን ያስፈልጋል።
🙏 ህይወትን ቀለል አደርጎ መኖር፣
🙏 መተንፈስ መቻል፣
🙏 እቃ ማንሳት መቻል፣
🙏 መንቀሳቀስ መቻል፣
🙏 ሰው ሰላም ማለት መቻል፣
🙏 ማውራት መቻል ... ትንሽሽዬ ነገሮች ሊደንቁን ይገባል። ማመስገን ይገባል። እኔ የበለጠ አመስጋኝ ሆኛለሁ።
ማመስገን፤ ህይወትን እንደተሰጠን ስጦታ መያዝ መቻል ተምሪያለሁ።
ሌላው ደግሞ ሰው ለራሱ ብቻ አይኖርም ፤ ከሰላምታ ጀምሮ እንዴት ነህ ? ደህና አደርክ ወይ ? ከማለት ጀምሮ ሰዎችን መደገፍ ከሰዎች ጋር ህይወትን ሼር አደርጎ መኖር እንደሚያስፈልግ ተምሪያለሁ፤ እነዚህ ነገሮች የበለጠ ትሁት (humble) ያደርጋሉ። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 2 ቀን 2018 ዓ/ም
(ከሱሉልታ ነዳጅ ማደያዎች)
• " 5፣ 6 ቀናት ወረፋ ላይ ቆመን እያለ 'ተነሱ' ይሉናል። ብር የሚከፍሉ ቀድመው ይሰለፉና እኛ ከኋላቸው ተሰላፊ እንሆናለን። እስከ ከ5 ሺህ እስከ 15 ሺሕ ብር ይቀበላሉ። ለምን ? ስንል ተደብድበናል። "
• " መኪና ይዘው እየመጡ የጸጥታ ኃይሎች ናቸው ብር እየተቀበሉ ድርጊቱን የሚፈጽሙት፤ ከአንድ መኪና 15 ሺሕ፣ 10 ሺሕ፣ 5 ሺሕ እንደ መኪናው መጠን እየተቀበሉ ሰልፍ ያልያዘ ተሽከርካሪ ነዳጅ እንዲቀዳ ይደረጋል። ለምን ? ስንል በዱላ ተደብድበናል። "
• " አንድ ፖሊስ ጋቢና ይቀመጥና 'የግዳጅ፣ የኮሪደር'፣ 'የፈጣን ፕሮጀክት መኪና ነው' ይላል። ግን የፈጣን ፕሮጀክትም ሆነ ሌላ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የሚቀዱት በቦቴና በበርሜል ነው። "
• " መኪና ለምንድን ነው ያለሰልፉ አልፎ የሚቀዳው ? ብዬ ስጠይቅ፣ ከተደበደቡት ውስጥ አንዱ ነኝ። "
• " አንድ ፖሊስ ጋቢና ይቀመጥና 'የግዳጅ፣ የኮሪደር'፣ 'የፈጣን ፕሮጀክት መኪና ነው' ይላል። ግን የፈጣን ፕሮጀክትም ሆነ ሌላ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የሚቀዱት በቦቴና በበርሜል ነው። "
• " ማደያ ላይ 'ስርዓት አስከባሪ ነኝ' ብለው የሚቀርቡ አካላት ሊፈተሹ ይገባል። ህግን ከለላ አድርገውና ዩኒፎርም ለብሰው ሌላ ተግባር ሲፈጽሙ አሉ እውነታው ይኸው ነው። "
• " ያልተሰለፉ አሽከርካሪዎች እንደመጡ ቀድተው ይሄዳሉ፤ ለዚህ እንደ መኪናው አይነት 20 ሺ ፣ 30 ሺ ለትራፊክ፣ ለጸጥታ አካላት ጉቦ ይሰጣሉ። አንዳንድ የጸጥታ አካላት ሳይቀሩ ከኋላችን የተሰለፉትን ራሱ 'ብር አምጡ ያለ ወረፋችሁ እናስገባችሁ' ይላሉ።"
• " ቀበሌ ላይ ያለ አንዳንድ የጸጥታ አካል የራሱን ጎሮሮ ከመዝጋት ውጭ ለኛ ሀዘኔታ የለውም። "
ተጨማሪ ያንብቡ 👇
www.facebook.com/61588053582297/posts/122109604119268452/?app=fbl
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 2 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
Reviews channel
4 total reviews
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
𝗔𝗕𝗖 𝗡𝗘𝗪𝗦 𝗔𝗠𝗛𝗔𝗥𝗜𝗖 is a Telegram channel in the category «Новости и СМИ», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 814 subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 17.4, with 4 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 2.4 ₽, and with 5 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий