
🌸 May Sale Weeks on Telega.io
Up to 70% off + 3.5% extra discount with promo code 4C8C39F0!
Go to Catalog
12.5

Advertising on the Telegram channel «ፍቅር እና ግጥም 🇪🇹»
5.0
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$18.00$18.00local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
Betty እባላለሁ እድሜ 23 ነው በጣም ቆንጆ እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል አስተናጋጅ ነኝ
በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት
see more....
136
21:06
16.05.2025
imageImage preview is unavailable
Wallpaper ወይስ Profile ይፈልጋሉ? 😍
196
21:00
16.05.2025
💙 የልቤ ትርታ 🔸
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️
#ክፍል_1️⃣0️⃣
🖌...ነገሩ አስገራሚም አስደንጋጭም ነው አስደንጋጩ ጌዲዮ አይመጣም ብለው ለደመደሙት ነው አስገራሚው ክስተት ደግሞ የመቅደስ ህልም እውን መሆኑ ነው።
.
....ለካ ነገሮች ሲዘበራረቁ ቦታ ቦታቸውን ሊይዙ ነው የሚባለው እውነት ነው።ጌዲዮ ካመጣችው ባጃጅ ሲወርድ እውን እሱ አይመስልም በጣም ከስቶ ፊቱ ጠቁሯል ምግብ አሳይተው እንደነሱት ህፃን ብብት ብሏል ፀጉሩ ተበጥሮ የሚያውቅ አይመስልም ልብሱም ዝርክርክ ብሏል ብቻ ባጭሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳይሆን የጎዳና ተዳዳሪ መስሏል ተማሪው ተገርሞ ለወሬ ከመቸኮሉ የተነሳ ቀስ ብለው ፎቶ አንስተውት በሚሴጅ መቀባበል ጀመሩ ባንዴ ግቢው ተዳረሰ ደስ ያላቸው እንዳያቅፉት እንኳን ደና መጣህ እንዳይሉት ይፈሩታል በመምጣቱ የተበሳጩት ደግሞ ቢችሉ መልሰው ቢያባርሩት ደስታቸው ነበር።.......
በዚህ ሰአት መቅደስ እራሷን አሟት ተኝታ ነበር እነሰአዳም አሉ። የመቅደስ ስልክ ሲጮህ ዝም አለችው ከዛም ሚሴጅ ገባ ብርሀንም ለምን አታዪውም አለቻት መቅደስም እራሷን ይዛ እንዳቃታት አመልክታ አንቺ እዪው አለቻት ከዛም ስትከፍተው ጌዲዮ የመምጣቱ ዜና ነው ብርሀን ሳታስበው በደስታ ጮኸች እነሱም ደንግጠው ምን ሆንሽ አሏት እሷም ነገረቻቸው ግን አላመኗትም ከዛም ፈጠን ብላ ፎቶውን አሳየቻቸው መቅደስ ከማየቷ ከመኝታዋ ወርዳ በለሊት ልብሷ ጫማ እንኳን ሳታደርግ በረረች እነሱም ተከተሏት...
.......ወይ ፍቅር
......ዞር ብላ ግራ ቀኝም አላየችም ቀጥታ እንዳየችው በራ ዘላ ተጠመጠመችበት እራስ ምታት የተባለ ተረሳ ጌዲዮ ትርታው ጨመረ ለማንም ተሰምቶት የማያውቅ ስሜት ለሷ ስለሚሰማው እንደማግኔት ስቦት እሱም አቀፋት ብዙ ተማሪ በሁኔታቸው አለቀሰ ብርሀንና ሰአዳማ ተቃቅፈው ነው ያለቀሱት ጓደኛ መታደል ልክ እንደነሱ ነው ደስታዋ ደስታቸው ሀዘኗ ሀዘናቸው። ሌሎቹም ፎቶ እያነሱ በ ፌስቡክ ይለጥፏቸው ጀመር ግን አዎ ተቃቅፈው ላያቸው እውነት ያጓጓሉ እናም ለደቂቃም ቢሆን ናፍቆታቸውን አስታገሱ ሁለቱም የደስታ እንባ ተናነቃቸው ግን ልትለቀው ስታስብ ፈራች ከዛ እየተቅበጠበጠች ደስታዋን ለመደበቅ እየሞከረች ካንገቱ ስትላቀቅ በሳቅ ተሞልታ አይናይኑን እያየች ውይ ጌዴ ይሄን ያክል ጊዜ የት ሄደህ ነው አለችው።
.....እሱም በስስት እያያት ዝም አላት ቀጠለች በመምጣትህ ደስ ብሎኛል እንኳን ደህና መጣህ አለችው እሱም አመስግኗት ቦርሳውን ይዞ ወደ ማደሪያው ሄደ።
........ጌዲዮ እንዲህ ጉስቁል ያለው በናፍቄቷ በፍቅሯ ነው ከሄደበት ቀን ጀምሮ ካንድ ቤት ወጥቶ አያውቅም ከሷ ሌላ ምንም አይታየውም ነበር በርግጥ በፊትም ማንንም ባያናግርም እሷን ሲለይ ግን ብሶበት አንድ ክፍል ውስጥ ማልቀስ ባለቀሰና እራሱን ባስጨነቀ ቁጥር በሽታው እየተነሳበት ከመቅደስ በላይ ጌዲዮ ተጎድቷል ትላንት ግን እራሱን መቆጣጠር ሲያቅተው የመጣው ቢመጣ የማንም ብትሆን አይኗን ባይ ይሻለኛል ብሎ ነው ገና በለሊት ጅማን የረገጠው።
......በውነቱ መቅደስ ስታቅፈው በህልም አለም ውስጥ ያለ ነበር የመሰለው ነገር ግን ሲለያት በውኑ መሆኑም ሲታወቀው ታፍቅረው አታፍቅረው ባይገባውም ደስታውን መቆጣጠር አቅቶ አለቀሰ።
........መቅደስም ስለቷ ሰመረ እሷም እንደሱ ማፍቀሩን ባታውቅም በደስታ ሰከረች።
.....ይሄንን የሰሙት መምህር ያሬድ ወይንሸት ዮናስም በንዴት የሚይዙት የሚጨብጡት አጡ።
.....የጅማ ዩንቨርስቲ እሁድም ስለሆነ ገና በጠዋቱ ድምቅምቅ አለ።
.......የመቅደስንና የጌዲዮን ደግሞ የመገናኘት ደስታ እነብርሀን ባንድ ለማድረግ አሰቡ በመቀጠልም ከጌዲዮ የዶርም ጓደኞች ጋር በመነጋገር ገንዘብ አዋጡ ብርሀን የሀብታም ልጅ ስለሆነች ከሴቶች ከፍተኛውን ወጪ የሸፍነችው እሷ ነች ከወንዶች ደግሞ በለጠው ወይንሸትን ሲነግሯት በጣም ስለተቃጠለች ግን እንዲያውቁባትም ስለፈለገች ብሩን አዋጣለሁ ፓርቲው ላይ ግን አልገኝም ሌላ ቀጠሮ አለኝ አለቻቸው ሰአዳም አረ ብር በሽ ነው አንፈልግም አለቻት።
......በርግጥ ለብዙ ጊዜ አብረውት ሲማሩ በዝምታውና በበሽታው የተነሳ ለማናገር ቢፈሩትም ዛሬ ግን ደፍረው ከማናገርም አልፈው ወስደው ፀጉሩን አስቆርጠው በራሳቸው ምርጫ አልብሰው አስጌጡት ጌዲዮ መጀመሪያ ሲነግሩት ውስጡ ደስተኛ አልነበረም ምክንያቱም ብዙ ጫጫታና ወከባ ያለበት ቦታ አይመቸውም ቡሀላ ግን መቅደስ እንደምትኖር ሲነግሩት እሷ ካለች የትም ይመቸኛል በሚል ሀሳብ ፍቃደኛ ሆነ።
.
.....መቅደስም ሲነግሯት ደስታዋ እጥፍ ሆነ እሷንም እንደሱ አስዋቧት
......ከዛም የሚገርም ፓርቲ ሆነላቸው በርግጥ አንድ ላይ ባይሆኑም ግን ባይን እየተሰራረቁ አንዳንዴ ደግሞ ደፍራ እየሄደች እያናገረችው ምሽቱን ቦረቁበት ግን ጌዲዮ ያመዋል ብለው ሰግተው ነበር እሱ ግን እንኳን ሊያመው የህመም ስሜትም አልተሰማውም ሁሉንም ያዝናና ዋው የሚያስብል ምርጥ ምሽት አብረው አሳለፉ...
🔻ክፍል 1️⃣1️⃣ ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
481
19:28
16.05.2025
ያዝናናኝን ላጋራችሁ #እባቡ_እና_እኔ
አውን ከመሸ ወደ 3ሰአት አካባቢ በክፍሌ ውስጥ ፊልም እያየው እያለ የጎረቤታችንን ኡኡኡኡ ድረሱልኝ እባብ እባብ 🐍🐍.... የሚል ጩኸት ሰማው፥ ወዲያው ትልቅ እንጨት አንስቼ እየሮጥኩ ቦታው ላይ ስደርስ😳😳ማጋነን አይሁንብኝ እና እስከ ዛሬ ካየዋቸው ሁሉ በጣም ትልቅ የሆነ እባብ፥የድሮ አብሮ አደጌ የአሁኗ crush-a የጎረቤታችን ልጅ ላይ አፍጥጦ አንገቱን ቀስሮ ቆሟል፤
እኔ በደረስኩ በትንሽ ሰከንድ ውስጥ ጩኸቱን የሰሙ ከ6 ያላነሱ ጎረቤቶቻችን እያንዳንዳቸው ጣውላ እና ፍልጥ ይዘው ደረሱ፤ ታድያ እኔ ሆዬ ይሄን ሁሉ ሰው ስመለከት ዛሬ ደፋር፣ ጀግና እና ትክክለኛ ወንድ መሆኔን ለሷ የማሳይበት ቀን ነው፥ ይህን እባብ መግደል ያለብኝ እኔ ነኝ ብዬ ወሰንኩ(በውስጤ)
ከዚያም ወደ እባቡ በመጠጋት በያዝኩት ዱላ ሶፋውን መታ መታ አድርጌ እባቡ ፊቱን ወደኔ እንዲያዞር አደረኩት እና ለ Crush-a ከነበረችበት ቦታ ቀስ ብላ ወደ ውጪ እንድትወጣ ነገርኩዋት፤ የሚገርመው ደግሞ ይሄ ሁሉ ሰው መቶ እንኳን እባቡ ንቅንቅ አላለም አንገቱን ወደ እኔ አዙሮ ከማፍጠጥ ውጪ🙄🙄 አሁን እኔ እና እባቡ ፊት ለፊት ተፋጠጥን፥ አንተ መጥፎ እባብ ዛሬ የመጨረሻ ቀንህ ነው በእጄ ትሞታለህ እያልኩ እየፎከርኩ፥ ለጎረቤቶቼ ከ1 እስከ 3 እቆጥራለሁ 3 ስል ሁለችንም አንዴ እባቡን እንመታዋለን ብዬ ነገርኳቸው እና በቀስታ መቁጠር ጀመርኩ 1.....2.. ብዬ 3 ልል ስል ቡም መብራት ጠፋ😳😳💔💔 ሰዎች መብራት ጠፋ ነው ያልኩት ደንግጡ እንጂ (እናንተ እንዴት ሆናቹህ ካላቹኝ)
የደነገጥነው ድንጋጤ የገባንበት በር እንኳን በየት በኩል እንደነበር አስረሳን 💗😳 Guys የሰው ልጅ ያን ያህል ደንግጦ ራሱን እንደማይስት ያወኩት በዚሁ በራሴው research ነው፤ ከዛ እራሴን እባቡ ካለበት ቦታ ለማራቅ ስል የድንጋጤ ፍሪጁ ላይ እንደወጣው እራሱ ዘግይቶ ነው የገባኝ😁😁 ሌሎቹም እንደዛው.....
ከትንሽ ሰከንድ በኋላ በጣም ለስላሳ የሆነ ነገር እግሬን ሲነካኝ ተሰማኝ😳🙄 እባቡ ነው ብዬ immediately በያዝኩት ፍልጥ ስለው ወዲያው ወይኔ ወይኔ ጭንቅላቴን አህህህህህ ኡኡኡ እያለ አንዱ መጮህ ጀመረ😂 እኔም በሀይል ስሰነዝር ሰውነቴን መቆጣጠር ተስኖኝ ስለነበር ከፍሪጁ ጋር ተከነበልኩ በምኔ እንዳረፍኩ ሁላ አላውቅም ብቻ ቶሎ ብዬ ብድግ ለማለት የምደገፈው ነገር ለመፈለግ እጄን ስዘረጋ የሆነን ሰው 🦶እግር ነካው፥ እሱም እንደኔው እባብ መስዬው ነው መሰል መጠኑን በማላውቀው በትልቅ ጣውላ ሰረበኝ🏸 ኧረ ምን ሰረበኝ ብቻ ይሄ cricket 🏏የሚሉት የህንዶች ጨዋታ አለ አይደል እሱን ነው የተጫወተብኝ ብቻ ምኔን እንደመታኝ ባላውቅም ሽንቱን በጣም ወጥሮት እንደሸና ሰው ኡፍፍፍፍፍ ነው ያስባለኝ...
ኡፍፍፍ ማለቴን ሳልጨርስ መብራት መጣ💡 Guys እኔ ካልገደልኩ ስል የነበርኩት ልጅ እንዴት ከቤቱ ውስጥ እየሮጥኩ እንደወጣሁ አጠይቁኝ 🏃♂🏃♂🏃♂
መልዕክት፦ ድፍረት ጨለማ ውስጥ የለም & መብራት ሀይል ደግሞ እምታጠፋበትን ሰአት ምረጡ Please
1176
11:30
16.05.2025
💙 የልቤ ትርታ 🔸
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️
#ክፍል_9️⃣
...🖌ምሽቱ በጭፈራ ቅልጥ ብሏል መቅደስ እራሷን አታውቅም ከዮናስ ጋር ታብዳለች ትጨፍራለች ትዘላለች ታቅፈዋለች ብቻ የዮናስ ጓደኞች መሸነፋቸውን አመኑ መዳኒት ጠጥታ መሆኑን ማንም አልጠረጠረም ግን ውርርዱን የሚያሸንፈው አብረው እንዳደሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ሲያቀርብ ነው ለዚህም ቀደም ብለው ከ ወይንሸት ጋር ዝግጅት አርገዋል።
...........ከዛም አቅፎ ወዳልጋ ክፍል ወሰዳት ስልኩ ደጋግሞ ይጮሀል ግን ብዙ ወንዶች አድንቀው ያላገኙት ገላ መዳፉ ላይ መሆኑን እያሰበ ሊያነሳው ፍቃደኛ አልነበረም መቅደስ በዛ ሰአት ምንም ቢያረጋት እራሷን አታውቅም ተዘርራለች ሌላ አለም ውስጥ ነች እሱም ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ይሄኔ ነው አለ ባንድ በኩል የውርርዱ ከፍተኛ ገንዘብ ሌላው አስደማሚው የመቅደስ ገላ ደስ አለው ከዛም ልብሱን ሲያወላልቅ ስልኩ ድጋሚ ጮኸ ተናዶ ሊዘጋው ሲያይ አሁን ካሰበው የውርርዱ ገንዘብ ሁለት እጥፍ የሚበልጥ ቢዝነስ ነው ዮናስ በብር ቀልድ አይወድም ሲኦል ብር አለ ቢባል እንኳ ገነትን ትቶ ሲኦል እንደሚገባ አያጠራጥርም ከዛም ይህንን ጨዋታ ለነገ ቀጠሮ ከራሱ ጋር ያዘ መቅደስንም ግቢ ድረስ አድርሷት ወደ ተጠራበት ቢዝነስ ሄደ።
.........ጠዋት ይህንን ወሬ ለወይንሸት ሲነግራት በጣም ተበሳጨች ቆይ እጅህ የገባን እድል አሻፈረኝ ብለክ ድጋሚ ትላለህ አለችው ዮናስም ከዚኛው የዛኛው ቢዝነስ ይበልጥ ነበር ስለዚህ የሚቀድመውን አስቀደምኩ አላት ወይንሸትም ታዲያ እንዴት ብዬ ነው ድጋሚ የማሳምናት በዛ ላይ ትላንትና ለምን ጥለሻት ሄድሽ ሲሉኝስ ምንድነው መልሴ ብላ ጠየቀችው እሱም ሴት ብልሀት አታጣም ይባል የለ ሴትነትሽን አንዳንዴ እንኳን ተጠቀሚበት ብሏት ሄደ።
...........የፈራችው አልቀረም ወደ ዶርም ስትገባ መቅደስ ታማ እነ ብርሀን እያስታመሙ ደረሰች ሰአዳ ልክ ስታያት ደሟ ፈልቶ ቆይ አንቺ መቼ ነው አደራሽን የምትወጪው አለቻት እሷም አይን አውጥታ ምን አረኩ አለች ይሄኔ ብርሀንም ቦግ ብላ ምን ማለት ነው የወሰድሻት እኮ ጭንቀቷን እንድትረሳ ላዝናና ብለሽ እንጂ አስክረሽ ሜዳ እንድትጥያት አይደለም።
.......ወይንሸትም ውሸቷን ጨማምራ እየውላችሁ መጀመሪያ ደና እየተዝናናን ነበር ከዛም ካልጠጣሁ ብላ አስቸገረችኝ ምንም ማረግ ስላልቻልኩ ሰጠኋት ከዛም መስከር ጀመረች ይሄን ጊዜ ዮናስን አየችው ከሱ ጋርም ካልጨፈርኩ ብላ እሪ አለችብኝ ደስታዋን ስለሆነ የምፈልገው እሺ አልኳት ከዛም ተመቻቹ መቅደስ ደንግጣ ከተኛችበት ተነሳች ምንድነው የተመቻቸነው አለቻት ወይንሸትም አስመሳይ ሳቋን በፌዝ መልክ ስቃ ማለት አንድ ላይ መደሰት መጨፈር ጀመራችሁ እሱም አብራኝ ትሁን እሸኛታለሁ ሲለኝ ያው እንደውስ ከኛ በላይ ውለታ ውሎልሽ የለ አብራችሁ እንድትሆኑ ትቼ ከፍቅረኛዬ ጋር ሌላ ጭፈራ ቤት ሄድን አለቻቸው ሁኔታው ቢያጠራጥራቸውም 50%አመኗት።
.........መቅደስ እንደበፊቱ መሆን ተስኗታል በደንብ አትበላ አትጠጣ አትማር አትተኛ ውበቷ ባይካድም ጉስቁል ብላለች።
የጌዲዮ አለመምጣት አድራሻውም መጥፋቱን ሙሉ ለሙሉ አመነች።......በዚህ ከቀጠለች ትምርቷን ማቆሟም የማይካድ ነው በርግጥ ጌዲዮ ከሄደ ሁለተኛ ሳምንቱን ያዘ
.......ወይንሸት አሁንም እኒድ እንዝናና የሚል ጥያቄ ለመቅደስ አቀረበች መቅደስም ጓደኞቿም አልተድማሙም ብንሄድ እራሱ ሁላችንም አሏት...... ፍፁም እንደትላንቱ ለማሳመን ጣረች የሚያምናት ግን አጣች።.....የዮናስም የወይንሸት እቅድ ግብ ሳይመታ ቀረ።
...........ዛሬ ደግሞ ቀኑ ሌላ ነው ለመቅደስ አፍቃሪዎች ሀዘንን አለማመንን ስቃይዋን ተረድተው ላዘኑላት እና ለራሷ ለመቅደስ ትልቅ የምስራች ቢባል ማካበድ አይሆንም...
🔻ክፍል 1️⃣0️⃣ ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
1480
17:02
15.05.2025
💙 የልቤ ትርታ 🔸
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️
#ክፍል_8️⃣
...🖌መቅደስና ሰአዳ የጌዲዮን አድራሻ ለመጠየቅ ወደ ቢሮ ሄዱ ቢሮውን ሲያንኳኩ ይግቡ የሚል ድምፅ ሰሙ ከፍተውም ገቡ ሲገቡም ያጋጠማቸው አስተናጋጅ የመቅደስ አፍቃሪ መምህር ያሬድ ነው።መቅደስ በሰአቱ አልደነገጠችም ባለፈው በንዴት ተማሪ መሀል መቅደስ የሰደበችውን አስታውሳ ሰአዳ ግን ክው ነው ያለችው። መምህር ያሬድ መቅደስን ሲያይ እየተቅለሰለሰ እንዲቀመጡ ጋበዛቸው ተቀመጡ ምን ልርዳችሁ አላቸው በትህትና እነሱም የጌዲዮን አድራሻ ፈልገው እንደሆነ አስረዱት መምህር ያሬድ በጌዲዮ የተነሳ በሚያፈቅራት ሴት አንደበት ተሰድቧል በሷ ሳይሆን በሱ ቂም ይዟል እሱ ከሌለ የግሌ አደርጋታለሁ ብሎም አሰበ በውስጡም እንኳን ከዚ ግቢ ከምድረ ገፅም ይጥፋ ብሎ ተመኘ በመቀጠልም ነገ ፈልጎ እንደሚጠብቃቸው ነግሮ ልክ በዚህ ሰአት መጥተው እንዲወስዱ ቀጠራቸው መቅደስ ፈፅሞ ቂም ይዟል ብላ ስላላሰበች አመስግነውት ሄዱ።.......ልክ እንደሄዱለትም በርብሮ ፈልጎ ወዲያው አገኘው ከዛም ከሌላ ሰውም እንዳያገኙት አርጎ የጌዲዮን አድራሻ ሰነድ አርቆ ደበቀው።
..........በነጋታውም ክላሱዋን አቋርጣ ባላት ሰአት ቢሮው ሄደች በለሰለሰ ድምጿ ስጠኝ ብላ ጠየቀችው መምህር ያሬድም መቅዲ የእውነት በጣም አዝናለሁ ከትላንት ጀምሮ ሌላ ስራ አልሰራሁም ማለት ይቻላል ስፈልግ ግን ላገኘው አልቻልኩም መቅደስም ሙሉ ተስፋዋ ተሟጦ አላገኘሁትም ማለት አለችው እሱም መቅዲ የቻልኩትን ሞክሪያለሁ ግን ላገኘው አልቻልኩም ምንም ማድረግ አልችልም ሲላት እንባዎቿ ካይኗ እንደጅረት ያለማቋረጥ ይፈሱ ጀመር መምህር ያሬድም ከወንበሩ ተነስቶ አጠገቧ ሄዶ አቅፎ ባስመሳይ አንደበቱ አባበላት።.....ከቢሮ ስትወጣ ላያት ከለቅሶ ቤት ተመላሽ ነው የምትመስለው............
...ከዛም እየተመላለሽ ጠይቂኝ ስላላት እየተመላለሰች ወደቢሮው ትሄዳለች እያለቀሰች ትመለሳለች አንድ ቀንም እንዲሁ እያነባች ወደ ክፍል ስትገባ እነ ብርሀን ቁጭ ብለው እያጠኑ ነበር ምንም ሳታናግራቸው ተጠቅልላ ተኛች ብርሀን ግን ቀሰቀሰቻት እና ይህ ቆይ የያሬድ ተንኮልስ ቢሆን አለቻቸው ሰአዳም እኔም ጠርጥሪያለሁ አለች መቅደስም ተነስታ ቁጭ አለች ወይን እሸት ግን ምንም መናገር አልፈለገችም ግን እውነት ቢሆንስ ብላ ለማጣጣል እንዴ ምን ልሁን ብሎ ይህንን ነውር ይፈፅማል ስትል ወዲያው መቅደስ ባለፈው ይቅርታ ስላልጠየኩት አለች እነብርሀንም አዎ የሚል መልስ ሰጧት ከዚያም ያሬድ በማይኖርበት ሰአት ሄደው ሌላ መምህር ጠየቁ ያው ያሬድ ስለደበቀው ፈልገው ቢያስፈልጉትም ሊያገኙት አልቻሉም ወይንሸት ደስ አላት ሰአዳና ብርሀን ግን ከመቅደስ ጋር አብረው አዘኑ።
.........ወይንሸት እና ዮናስ ጌዲዮ ስለጠፋ መቅደስን እንዳሰቡት የጌሙ መሀል ላይ ማቆም አልቻሉም አሁን እሷ ማንንም ማግኘት አትፈልግም ልክ እንደጌዲዮ ብቸኝነትን መርጣለች ይሁን እንጂ ሙከራቸውን አላቆሙም ባለፈው ወይንሸት ማሳመን እንደከበዳት ለዮናስ ስትነግረው ቅድሚያ ብር ስለሰጣት ዝቶባታል እሷም ከዮናስ ከተጣላች ብዙ ገቢ እንደምታጣ ስለምታቅ ሙከራዋን አጠንክራ ቀጥላለች።
መቅደስ ጌዲዮን በብዛት የምታይበት ቦታ እየሄደች በተስፋና በናፍቆት ትጠብቀዋለች የወንዶች ዶርም መግቢያውን ከሩቅ ሆና ድንገት የምታየው እየመሰላት በስስት ትጠብቀዋለች ወድቆ የምታቅፈውን ታስታውሳለች እውነት ላያት ታስለቅሳለች ለካ ፍቅር እውነትም ሀያል ነው ማለትም የማይቀር ነው።....ፍቅርን ስላልፈለጉት አይለቅም ስለፈለጉትም አይዝም በቃ በፍቅር ወጥመድ ውስጥ መውደቅ ወደድንም ጠላንም የተፈጥሮ ህግ ነው ከዚ በፊት መቅደስ ካይስኩል ጓደኛዋ ፍቅር እንዲይዛት ትፈልግ ነበር ምክንያቱም ለሷ ከማንም በላይ ብዙ ነገር ሆኖላታል ብዙ ብዙ በቃላት የማይገለፅ ፍቅርን ሰቷታል ግን ፍቅር እንዲይዛት ስለፈለገች አልያዛትም ይኸው ዛሬ ግን ተራው ደርሷት በጌዲዮ ፍቅር እንዲህ እየታመመች ነው።.............ከሩቅ ሆነው ሲያዩዋት የነበሩ የግቢው ቦዘኔ ተማሪዎች ሊያስደነግጧት ተነጋገሩና አንድኛው ተማሪ ልክ እንደጌዲዮ አጎንብሶ ወደወንዶቹ ዶርም መግቢያ ሄደ መቅደስም በተስፋ ስትመለከተው የነበረው መግቢያ ጌዲዮን ያመጣው መሰላት ልጁም ልክ እንደጌዲዮ ተንፈራፍሮ ወደቀ መቅደስም ጨርቋን ጥላ ወደሱ እሮጠች ልክ ስትደርስም ልጁ በሳቅ ወደቀ ሌሎቹም እራሷን እስክትይዝ ሳቁባት እያለቀሰች ወደማደሪያዋ ሄደች አብዛኛው ተማሪ ግን አዘነላት እነዛ ቦዘኔ ተማሪዎች በሰሩት አሳፋሪ ስራ ተበሳጩ እውነት ግን የፍቅር አምላክ ጌዲዮን ያመጣላት ይሆን???????????
........ዶርም ስትገባ ብርሀንና ሰአዳ ሁኔታዋ አንጀታቸውን በልቶት አብረዋት አለቀሱ ወይንሸትም አሁን ተንኮል ለመስራት አመቺ ግዜ ላይ እንዳለች አስባ ብርሀንን እና ሰአዳን መቅደስን ማዝናናት እንደምትፈልግ ነግራ እነሱም እንዳይከተሏት አሳመነቻቸው ከዛም በስንት ልመና መቅደስን ላዝናና በሚል ፓርቲ ወሰደቻት ሀሳቧ ግን ማዝናናት ሳይሆን በመዳኒት አደንዝዛ ከ ዮናስ ጋር አንሶላ እንዲጋፈፉ ማድረግ ነው።ከዛም እንዳሰበችው ቀኑ ሄዶ ጨለማው ሲተካ የቀረበላት ለስላሳ ላይ መዳኒት ጨመረች እራሷንም ስትስት መጨፈር ማበድ ስትጀምርላት ፈረሱም ሜዳውም ያው ብላ ለዮናስ አስረክባ ከሹገር ዳዲ ጋር ተቃቅፋ ወጣች...
🔻ክፍል 9️⃣ ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
1700
20:47
14.05.2025
💙 የልቤ ትርታ 🔸
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️
#ክፍል_7️⃣
...🖌በቃ ጌዲዮ ሄደ አንድ ሁለት ተብሎ ሶስተኛ ቀን ተቆጠረ መቅደስ ግራ ገባት ከክፍል ተማሪ አንስታ እስከ ዳሬክተር እየተመላለሰች በምን ምክንያት እንደጠፋ ጠየቀች ግን መልስ ማግኘት አልቻለችም የጌዲዮ መጥፋት የዩንቨርስቲውም አሳሳቢ ዜና ሆኑዋል ምክንያቱም ጌዲዮ በጣም ተስፋ የተጣለበት ጎበዝ ተማሪ ነው።
........መቅደስ ምግብ አልበላ ውሀ አልጠጣ አለች ትኩረቷም ከትምርቷ ተነሳ ታመመች ምንም የግሏ ባይሆንም አቅፋ ስታስታምመው የራሷ ያደረገችው ያክል ስለሚሰማት ደስተኛ ነበረች ፍቅሯ የጋራ ባይመስላትም እሷ ግን አይኑ ነበር የፍቅር ምግቧ አሁን ግን ጠፋ ምክንያቱን እንኳን ሳታውቅ ተሰወረባት ብቸኝነት ተሰማት።
.......አሁን የዮናስ እና የወይንሸት ሀሳብ ተሳካላቸው የጀመረውን ጌም ለማሸነፍ አንድ እንቅፋቱን አስወገደ መቼም ከዚህ ቡሀላ ይመጣል ብሎ መገመት ከባድ ነው።
.........መቅደስ እራሱዋን አስራ ብቻዋን ዶርም ተኝታ በናፍቆት እየተብሰለሰለች ትገላበጣለች ከዛም እነሰአዳ መጡ በየቦታቸውም አረፍ አሉ ወይንሸት ግን ይህን የተወጣጠረ እርቃኑዋን ነች አትባል ለብሳለች አትባል ብቻ ለባብሳ መቀባባት ጀመረች እነብርሀን የመቅደስን ሁኔታ እያዩ ነው አያባብሏት ነገር ብዙ ብለዋት ማፅናኛ ቃል አልቆባቸዋል ደግሞ ያውቃሉ መፍትሄ እንጂ ምክር አይጠቅማትም.....
....ከዛም ሰአዳ ወደ ወይንሸት ዞራ ወይና ግን በአላህ ምናል ትንሽ እንኳን ሸፈን ያለ ነገር ብትለብሺ አለቻት እሷም አረ ይሄም እራሱ እረዝሟል ስትል ብርሀን እግዚኦ ታዲያ አንድኛሽን እርቃንሽን አትሄጂም ስትል መቅደስ በተዋጠው ድምጿ ግን የት ልትሄጂ ነው እንዲህ ሆነሽ አለቻት እሷም እእእ ፖርቲ ዛሬ እኮ እኔና ሚኪ የተዋወቅንበት አንደኛ ወራችን ነው አለች መቅደስም አይ ለወደፊትማ ሰላም ከተባባልሽው ወንድ ሁሉ ልደት ታከብሪያለሽ ብርሀን ሳቅ ብላ የት ይቀራል አለቻት።
ከዛም ወይና ወደ መቅደስ ከተኛችበት አልጋ ተጠግታ እንዳዘነ ሰው ቅልስልስ ብላ መቅዲ ግን ይሄን ጌዲዮን እረስተሽ ለምን ከዮናስ ጋር አዲስ ላይፍ አትጀምሪም እስከመች እንዲህ ተኮራምተሽ አለቻት እነብርሀንም ግራ ስለገባቸው አው እርሺው እሱ እንደሁ ጥሎሽ ሄዷል እራስሽን ማረጋጋት አለብሽ አሏት መቅደስም እናንተ ምን ነካችሁ ዮናስ እኮ ንፁህ ጓደኛዬ ነው ወይንሸትም ፈጠን ብላ እሱ ግን ያፈቅርሻል ስትላት ስልኳ ጮኸ በቃ መቅዲ አስቢበት ብላ ቦርሳዋን ይዛ ስልኳን እያናገረች ወጣች ከዛም እነብርሀን ወሬውን ሊቀጥሉ ሲሉ መቅደስ ይልቅ እኔም ስለ ጌዲ ያልጠየኩት አንድ የክፍሉ ልጅ አለ እሱ ጋር ልሂድ ብላ ተነሳች ሰአዳና ብርሀንም ተከተሏት።
...ሄደውም ሌላ ጓደኛውን አገኙ ይቅርታ ወንድም በለጠውን ፈልገን ነበር ሲሉት በሌ መቃሚያ ቤት ነው በዚህ ሰአት እዚህ አይገኝም ግን እኔም እዛው ልሄድ ድለሆነ ከፈለጋችሁ ልውሰዳችሁ አላቸው እነሱም ተስማምተው አብረውት ሄዱ።
በእውነት እዚህ መንደር መቃሚያ ቤት ቀርቶ ሱቅ እንኳን ያለ አይመስልም ብቻ እያሹለከለከ ወሰዳቸው ወደ ውስጥ ሲገቡ በጣም ተደናገጡ ውስጥ ያሉት እነመቅደስን እነሱ ደግሞ ተማሪዎቹን እያዩ ተፋጠጡ ግማሹ ጫት ይቅማል ግማሹ ሺሻ ያጨሳል ሌሎቹ ሲጋራ ቀስ ብለው ተቀመጡ ከዛም በትዝብት ቤቱን ይቃኙ ጀመር አብዛኞቹ የግቢ ተማሪዎች ናቸው ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚቅሙና የሚያጨሱም አሉ
ከዛም አንዷ መጣችና ምን ልታዘዛችሁ አለቻቸው በዚህ ሰአት ያመጣቸው በለጠውን ሊጠራ ሄዶ ነበር እናምአረ ምንም አንፈልግም አሉ ታዲያ ምን ልትሆኑ ገባችሁ ስትላቸው በለጥው ተያቸው እኔን ፈልገው ነው አላት
ከዛ አጠገባቸው መጥቶ ተቀመጠ ምን እንደፈለጉ ሲጠይቃቸው ስለጌዲዮ የምታውቀው ነገር ካለ ብለን ነው አሉት።
.......ስለሱማ እኔም በጣም ታስዝቤሻለሁ ያረግሽው ነገር እኮ ከንዳንቺ አይነት ሴት የማይጠበቅ ነገር ነው አላት መቅደስ ምን እንደምታወራ አልገባኝም አለችው ለማንኛውም ልወጣ ስለሆነ እየሄድን እናውራ አላቸው ከዛም ተነሱ
....ቀጠለ ልንገርሽ ጌዲዮ ትምርቱን የተወዉ ባንቺ ምክንያት ነው መቅደስ በጣም ደነገጠች ማፍቀሩን ባይገልፅላትም ያኔ ጌዲዮ ብቻውን ሆኖ ሲያወራ ከበር ቆሞ የሰማውን ሁሉ ነገራቸው።
.........መቅደስ እነ ብርሀንን ጠየቀች ማነው ማነው እንዲህ ያለው?? እኔኮ የወደኩት ብላ የወደቀችበትን ሁኔታ ነገረቻቸው እነሱም አንገት ደፉ ብርሀንም ሙሉ ግቢው እኮ ነው በሱ በሽታ መውደቅሽን ያወራው ስትል ታዲያ ለምን አልነገራችሁኝም ብላ ጮኸች ሌላ ህመም ጌዲዮ በሷ ሰበብ እንደሆነ አወቀች ትምርቱን የተወው...
በቃ ትምርትም አስጠላት ይኸው ክፍል ቁጭ ብላ ሀሳቧ ግን ሌላ ጋር ነው ከዛም አቋርጣ ወጣች ሰአዳም ተከተለቻት መቅደስ ግን ምን እየሆንሽ ነው ቢያንስ ለናት አባትሽ ለቤተሰቦችሽ አታስቢም የውጪ እድልሽን አሳልፈሽ እየተማርሽ ያለሽው እኮ ያስተማረሽን ህዝብና ሀገር ለመጥቀም ነው ከሁለት አጥ አትሁኚ እንጂ አላማሽን እንዴት ትዘነጊያለሽ ብላ ሰአዳ ተቆጣቻት መቅደስም እንባ ተናንቋት አቃተኛ አቃተኝ ምን ላርግ አልቻልኩም እንደውም እኔም አልማርም ስትል ሰአዳ መቅደስ ይሄ መፍትሄ አይሆንም ባይሆን ለምን አድራሻውን ፈልገን አንሄድም አለቻት ከዛም ተያይዘው አድራሻውን ለማግኘት ወደ ቢሮ ሄዱ...
🔻ክፍል 8️⃣ ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ
2054
17:27
13.05.2025
💙 የልቤ ትርታ 🔸
.
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️
#ክፍል_6️⃣
...🖌ጌድዮ መቅደስ የሱ በሽታ ተጋብቶባት ነው ካሉት ቡሀላ ሂወት አስጠልቶታል መኖር ሰልችቶታል በቃ ሰሞኑንማ በዚህ የተነሳ በሽታው ብሶበታል።....መቅደስ ግን ይህን የማይመስል ወሬ አልሰማችም ብትሰማማ ምንኛ ባዘነች ነበር ሆኖም አሁንም ከሱ አልተለየችም።
......ጌዲዮ ዶርም ውስጥ ሆኖ እንደለመደው እራሱን እየጠየቀ ብቻውን እያወራ ነው ለምን እማራለሁ? ማንን ልጠቅም? ማንን ልረዳ? ደግሞ እኔን ሰው ብሎ ማነው የኔን እርዳታ የሚፈልግ? ማንም ማንም የለም ማንም ከዛም ትምርቱን ለማቆም ወሰነ ቢሆንም ለራሱም የማይክዳቸው ሁለት እውነታዎች ከለከሉት አንድኛው ምክንያቱ መቅደስን አፍቅሯታል ሌላው አደራ አለበት አልቻለም በሁለት መንገድ ተጠመደ ከዛም ጮክ ብሎ መቅደስ ለምን አፈቀርኩሽ ለምን ቀረብሽኝ እያለ ይወቅሳት ጀመር ባዚህን ጊዜ ዶርም ውስጥ ማንም ባይኖርም በለጠው የተባለ የክፍሉ ተማሪ በር ላይ ቆሞ እየሰማው ነበር።
.......መቅደስ ስትወድቅ የተቦጫጨረው ፊቷ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋም አሁን ጤነኛ ነች ያው እንደተለመደው እሷ ሰአዳ ብርሀን ወይንሸት ሆነው ካፌ ቁጭ ብለው ሻይ ቡና እያሉ ነው ወይንሸት ፈፅሞ በፍቅር አታምንም እሷን የሚገዛት ገንዘብና መልክ ነው በዚህ ፀባይዋ ከሶስቱም ጋር አትስማማም በተለይ መቅደስ ሁሌ ሰው እንድትሆን ትመክራታለች እሷ ግን በቀኝ ሰምታ በግራ ታፈሰዋለች መጨፈር ሺሻ ጫት መቃም ከሹገር ዳዲዎች ጋር መውጣቱዋ የታወቀ ፀባይዋ ነው።እናም እየተጨዋወቱ እያለ ዮናስ እየተንጎባለለ መጣ...
ሁሉንም ሰላም ካላቸው ቡሀላ አብሯቸው ተቀመጠ ከዛም ግን ለምን ወጣ ብለን ምሳ አንበላም አላቸው ወይንሸት ተቅበጥብጣ እሺ አለች እነብርሀንም የግቢ ምግብ ስለሰለቻቸው ተስማሙ መቅደስ ግን ለመሄድ አልፈለገችም ቢሆንም በውለታ ስለታሰረች ፈገግ ብላ ጥያቄውን ተቀበለች።
.......ከዛም ይዟቸው ከግቢ ሲወጣ አሁንም ጌዲዮ አየ ዮናስ ተንኮሉ መቅደስ መቅደስን እየታከከ ነው የሚሄደው።ከጌዲዮ አጠገብ የነበሩ ሁለት ልጆችም አይተው ስለመቅደስና ስለዮናስ ማውራት ጀመሩ አንተ ግን መቅዲ ዮናስን አፈቀረችው አይደል? ... አረ አይመስለኝም ..ተው እንጂ ዮናስን እዚህ ግቢ የማታፈቅረው ሴት አለች ልትለኝ ባልሆነ...በርግጥ ቆንጆ የተባሉት ሁላ ያፈቅሩታል ግን እሱ የሚፈልጋቸው ግዜ ማሳለፊያ አይደል እንዴ?.....ባክህ መቅደስም ተከይፋበታለች ታስታውቃለች ጌዲዮ ለመስማት ተሳነው ከተቀመጠበትም ተነስቶ ወደለመደው ጫካ ሄደ ......
ዮናስ ምሳ ጋብዟቸው ሲያበቃ ለምን አንድ ሁለት እያልን ስንቀውጠው አናመሽም አላቸው ይህን ጊዜ ሰአዳ በሉ እኔን ሸኙኝ አለቻቸው መቅደስም አረ እኔም ጥናት አለብኝ አላመሽም አለች መቅደስ እንድትቀር ወይንሸትና ብርሀን ለመኗት እሷም አይሆንም አለች ከዛ ብርሀን መቅዲ ካላመሸች እኔም አልፈልግም አለች ከዛም በቃ ልሸኛችሁ ብሎ ወደ ግቢ ወሰዳቸውና ከወይንሸት ጋር ተመለሱ።
......ልክ እነመቅደስ ወደውስጥ ሲገቡ እነሱም መታጠፊያውን መንገድ ሲይዙ ወይንሸትና ዮናስ ተቃቅፈው እየተላፉ ሲላቸው እየተሳሳሙ መንገድ ጀመሩ ዮናስና ወይንሸት መቅደስ የማታውቀው ድብቅ ግንኙነት አላቸው ሁለቱም የጥቅም ሰው ስለሆኑ ይስማማሉ ባለፈውም መቅደስ የወደቀችው የጌዲዮ በሽታ ተላልፎባት ነው የሚለውን ወሬ ዮናስ ነው በወይንሸት አፍ ያስለኮሰው ምክንያቱም ሁለቱ እንዲለያዩ ይፈልጋል ዮናስ ጌዲዮንን በነገር ግቢውን ሊያስለቅቁት ለወይንሸት ብር ሰጥቶ አሳምኗታል።
......ይኸው በወይንሸት ስብከት በተደጋጋሚ ዮናስና መቅደስ እንዲገናኙ ሲገናኙም ጌዲዮ እንዲያይ እያደረገች ነው።
....ጌዲዮም የሚሰማው የመቅደስ እና የዮናስ የተቀናበረ የውሸት ፍቅር እውነት ነው ብሎ ሊቀበል እየተገደደ ነው።
....በተለይ ባለፈው አቅፎ ሆቴል ሲያስገባት ካየ ቡሀላ ትምርት በቃኝ እሷን እያየሁ ከምቃጠል ባቋርጥ ይሻለኛል ብሎ ከትምርቱ ሊሰናበት ወስኗል።
.........ጌዲዮ መቅደስን እንዳትጠጊኝ ስለኔ አይመለከትሽም ካላት ቀን ቡሀላ ዘወር ብላም እንዳላየችው ነው የሚያውቀው...አሁንም እራሱን ጠየቀ እውነት አፍቅራኝ ቢሆን አትንኪኝ ስላልኳት እኔን ትታ ሌላ ወንድ ጋር ባትሄድ ነበር አለ።
ከዛም ፍቅሯን መቋቋም ሲያቅተው ካይኗ ብርቅ ይሻለኛል ብሎ ትምህርቱን ሊሰናበት ወደደ መፅሀፎቹን ብቻ ሰብስቦ ለማንም ሳይናገር ወደ መጣበት ሊመለስ ግቢውን ለቆ ወጣ ልክ የግቢውን በር ሲያልፍ አደራ መብላቱን ፍቅሩን ማጣቱን አስታውሶ በቆመበት ወደቀ መቅደስም ከሩቅ አይታው እየሮጠች መጥታ በፊት እንደምታደርገው ክርቢት ምናምን አጭሳ ሰውነቱ ሲረጋጋ ሳይነቃ ልታመልጠው ልትነሳ ስትል አድርጎት የማያውቀውን ወዲያው ነቃ መቅደስ ውሀ ሆነች እንዳይመታት ሁለት ጉንጮቿን በእጆቿ ያዘች ተንቀጠቀጠች ጌዲዮ ግን በልቡ አይኖችሽ ስንቅ ይሁኑኝ ብሎ ፍዝዝ ብሎ አያት አይኖቹ እንባን አፈሰሱ መቅደስ ሳታውቅ ፍቅሯ ተሰናብቷት መንገዱን ቀጠለ መቅደስም ሁኔታው ግራ አጋብቷት ሳታውቀው በቆመችበት ባይኖቿ ሸኘችው...
🔻ክፍል 7️⃣ ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
2494
17:00
12.05.2025
◆ሕይወት በለውጥ እንጂ በዕድል አትሻሻልም። ሰው የምሩን ካሰበ ተዓምረኛ አልያም ሰበበኛ መሆን ይችላል ይላሉ የስነልቦና ምሁራን። በርካታ ወጣቶች ካሉበት ሁኔታ የተሻለ ነገርን ለምን አላስመዘገባችሁም ሲባሉ ዕድሉን ስላላገኘሁ ይላሉ። (በእርግጥ ለውጥን የሚፈጥረው እድል ነው)። ለለውጥ ያልተዘጋጀ ሰው ግን ምንም ያክል ዕድል ቢሰጠው ዕድል ሰጪውን ያማርራል እንጂ አንዳች ነገርን አይፈጥርም።
የሀብታም ልጅ ስለሆንክ ጥፋትም ልማትም ዕድልህ ነው። የምሁር ልጅ ስለ ሆንክ ለማወቅም ለተራ ሰውነትም ዕድሉ አለህ። የመሪ ልጅ ስለ ሆንክ መምራት አልያም መመራት ዕድልህ ነው። ራስህን ለማሻሻል ለለውጥ መሻት ወሳኝ ነው። ምርጫህን በትኩረት ተመልክተህ ፈቃድህን ተጠቅመህ ራስህን ለለውጥ ካላዘጋጀህና በመንገዱ ካልተገኘህ ሕይወት በዕድል ብቻ አትቃናም። ዕድል ሕይወትን ታሻሻል ዘንድ ለጥቂቶች የምትሰጥ ቢሆንም ለውጥ ግን ለአጠቃላይ የሰው ልጅ የተሰጠ እኩል የመሆኛ ክፍት መንገድ ነው።
2539
03:31
12.05.2025
💙 የልቤ ትርታ 🔸
❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️
#ክፍል_5️⃣
...🖌መቅደስ ልትመለስ ስትዞር ቀሚሷ ጠልፏት እየጮኸች ቁልቁለቱን ተንከባለለች።........ሶስቱ ጎረምሶችም ድምጿን ሰምተው ከተቀመጡበት በፍጥነት ተነሱ ግን ወዲያው ፀጥ ስላለች ያለችበት ቦታ ጠፋቸው ግራ በመጋባት እየዞሩ ፈለጓት ከዛም አይ ጆሯችን ነው ብለው ወደ በርጫቸው ሲመለሱ ድጋሚ በስተ ኋላቸው ድምፅ ሰሙ እየተሯሯጡም ሲሄዱ መቅደስ በሾክ ፊቷ ተቦጫጭሮ ደም ለብሷል መነሳት አቅቷት እያቃሰተች እየተፍጨረጨረች ነው እንዲህም ሆና ውበቷ እንኳን ለመረቀነ ለማንም አሳልፎ ይሰጣል ሶስቱም ሊበሏት ጎመጁ ስቃዩዋና ለቅሶዋ አልታያቸውም እርስ በርስ ተነጋገሩ አቅፈውም ወደ ተቀመጡበት ቦታ ወሰዷት መቅደስም ሊደፍሯት እንደሆነ ሲያወሩ ስትሰማ ጭንቅላንቷ ከመታት ድንጋይ ጋር ተደምሮ እራንሷ ሳተች።
............ጌዲዮ በዚያ ሰአት ጥናቱን ጨርሶ ሳያያት አልፏቸው ወደ ግቢ ሄደ.።
....... ጎረምሶቹም እኔ ልቅደም እኔ ልቅደም እያሉ መጨቃጨቅ ጀመሩ ከመቅፅበት ያንድኛው ስልክ ጮኸ በፍጥነት አንስቶ ሄሎ ዮኒ ሲል ምኑ ጋር ናችሁ አለ ልጁም የባለፈው ቦታ ነን ደግሞ ዛሬ በተቀደሰው ማእዳችን ላይ የተቀደሰ የምስራች ይዘን ነው የምንጠብቅህ አለውና ስልኩን ዘጋው ዮናስን በጣም ስለሚፈሩትና ስለሚያከብሩ ሊጠብቁት ተስማሙ።
.......እነብርሀንም የመቅደስ ያለወትሮ ሳትናገር መጥፋት አሳስቧቸው ስልኳን ደጋግመው እየሞከሩ ነው ቢሆንም ስልኳ ካገልግሎት ክልል ውጪ ነች ይልላ አሁን ያላቸው አማራጭ ትሄዳለች ብለው ያሰቡበት ቦታ እየሄዱ መፈለግ ነው እስካሁንም የቆዩት እንደለመደባት ጌዲዮንን ተከትላ ነው ብለው ነበር አንሁ ደግሞ ጌዲዮን ግቢ ውስጥ አዩት
........ዮናስ ጓደኞቹ ከሚቅሙበት ቦታ ሲደርስ መቅደስን አያት ባይደነግጥም በጣም እንደደነገጠ ሆነ መቅደስን ከጁ መዳፍ ለመጣል ትልቅ ወጥመድ አገኘ በርግጥ ዮናስ እንደ መላእክት ቀርቦ የልቡ ሲደርስ ሰይንጣ መሆን የለመደው ድርትጊ ነው።ጓደኞቹም በሁኔታ ተገርመው ምን ታቃለታህ እንዴ አሉት እሱም አይ አላቃትም ግን የግቢያንች ተማሪ ናት ሲል ሳቁበትንና አረ ዮኒ ላሽ እርኩስ ደርሶ ፃድቅ ልንሁ ሲል አምያርትበም አሉት ዮናስ ግን እንቢ እንምይማሉት ስለሚያውቅ ዛሬ ማታ በርድ በርድ የሆኑ ቺኮችን አመጣላችኋለሁ መቅደስን ግን ለኔ ተዉዋት አላቸው ሆኖም ሁኔታው ቢያስገርማቸውም ብምዙ ሳይከራከሩ በሀሳቡ ተስማሙ።............ዮናስም እዚያው እንድትነቃ ስላልፈለገ አቅፎ ወደ ሆስፒታል ይዟት ሄደ።
.........ቀኑ ምሽቱን ተካ የመቅደስን መሰወር ሙሉ ግቢው ሰማ ትኖራለች ተብሎ የታሰበበት በሙሉ ተፈለገች ግን አልተገኘችም የበላት ጅብ አልጮህ አለ ጓደኞቿ በጣም ተጨናነቁ........
......መቅደስ ሆስፒታል በገባች ግማሽ ሰአት ውስጥ ነቃች ስትነቃ የምታየውን ማመን አቃታት ከዛ አስፈሪ ጫካ ወጥታ ሆስፒታል ከነዛ የሰው አውሬዎች ተርፋ እራሷን ከዮናስ ጋር ስታገኘው በህልሟ መሰላት እውነታውን ለማረጋገጥ ቸኮለች ዮናስም ጭንቅላቷን በጆቹ እየደባበሰ አይዞሽ አታስቢ ተርፈሻል አላት መቅደስም ይህ እንዴት ሆነ እዛስ ጫካ እንዴት መጣህ እንዴትስ ምንም አልሆንኩም ስትል ጥያቄ ደርድራ ጠየቀችው ዮናስም በገዳይ ምላሱ የሌለ ውሸት ጨማምሮ ብዙ ችግር ደርሶበት እንዳዳናት ነገራት ነግሮም አሳመናት መቅደስም በደስታ እያመሰገነች አቀፈችው።
.....በጣም ቆስላ ስለነበር ለትንሽ ቀን እንደልብ መንቀሳቀስ አትችልም ለዛሬ እዚሁ ትደር ብላ ነርሷ ለዮናስ ነገረችው።እናም እዚያው አብሯት አደረ።
........እውነት ለመናገር ጌዲዮ መጥፋቱዋን ከሰማበት ሰአት ጀምሮ በሀሳብ ሲብሰለሰል መሄጃ ጠፍቶት ሲቁነጠነጥ እንዲችው እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር አደረ።...... ጓደኞቿም ቢሆኑ ሲፈልጓት ነው ያደሩት
........ጠዋት ዮናስ መቅደስን በኮንትራት ታክሲ ይዟት መጣ ከዛም አውርዶ እስከ ሴቶች ዶርም ድረስ ተሸክሟት ሄደ ጌዲዮም ከሩቅ አያቸው ጓደኞቿም እየተሯሯጡ ተቀበሉት ምን ሆና እንደሆነም ጠየቁት እሱም ጫካ ውስጥ ወድቃ እንዳገኛት ነግሯቸው አስተዛዝኖ እግዚአብሔር ይማርሽ ብሏት ተመለሰ መቅደስም ዮኒ አለችው እሱም ቶሎ ተመልሶ ፊትለፊቷ ቆመ መቅደስም ምን ብዬ እንደማመሰግንህ አላቅም ቃላቶች ያጥሩኛል ብቻ ፈጣሪ ውለታህን ይክፈልልኝ ብላ ጥምጥም ብላ አቀፈችው።ጌዲዮ አሁንም እያያቸው ነው መተቃቀፋቸው ሳይሆን ምን እንደሆነች ለማወቅ ነበር የጓጓው ።ሆኖም
...... መቼም ወሬ የማያጣ ሰው እንዲህ ሲባል ወሬ ተለኮሰ የመቅደስ መውደቅ የጌዲዮ በሽታ ተላልፎባት ነው እያለ ወሬ ከዛ ከዚ ሲወረወር ደጋግሞ የጌዲዮ ጆሮ ገባ ጌዲዮም እውነት ይሆን እንዴ ብሎ አነባ እራሱን የማይረባ የማይጠቅም ሰበበኛ አድርጎ ቆጠረ ለምን ፈጠርከኝ ብሎ ፈጣሪውን አማረረ ........በቃ ሂወት እጅ እጅ አለችው እራሱን አገለለ ...
🔻ክፍል ስድስት ከ1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ።
2604
17:04
11.05.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeennew@******.io
On the service since June 2022
13.04.202523:31
5
Everything is fine. Thank you!
New items
Channel statistics
Rating
12.5
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
1
Subscribers:
14.4K
APV
lock_outline
ER
--%
Posts per day:
2.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий