
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
7.1

Advertising on the Telegram channel «Islamic movie»
Other
Language:
Amharic
0
0
🔑🔑🔑ይህ ቆየት ያሉ እና ተወዳጅ የሆኑ Islamic ፊልሞችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበት ቻናል ነው። ሙሉ ክፍሎቹን ለማግኘት👇👇👇 📢 or ያናግሩን እንዲሁም ፈልጋችሁ ያጣችሁትን ወይም ምትፈልጉትን Islamic movie እኔጋ ብቻ ያገኛሉ
Share
Add to favorite
Buy advertising in this chat
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Forwards
Delete after 24 hours, pinned for the duration of the post
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$12.00$12.00local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
يقول شيخ الإسلام :
وَنَظِيرُهُ فِي الدُّنْيَا مَنْ نَزَلَ بِهِ بَلَاءٌ عَظِيمٌ أَوْ فَاقَةٌ شَدِيدَةٌ أَوْ خَوْفٌ مُقْلِقٌ؛
فَجَعَلَ يَدْعُو اللَّهَ وَيَتَضَرَّعُ إلَيْهِ حَتَّى فَتَحَ لَهُ مِنْ لَذَّةِ مُنَاجَاتِهِ مَا كَانَ أَحَبَّ إلَيْهِ مِنْ تِلْكَ الْحَاجَةِ الَّتِي قَصَدَهَا أَوَّلًا؛
وَلَكِنَّهُ لَمْ يَكُنْ يَعْرِفُ ذَلِكَ أَوَّلًا حَتَّى يَطْلُبَهُ وَيَشْتَاقَ إلَيْهِ.....
«مجموع الفتاوى» (1/ 28)
1
15:26
23.08.2025
أَلَآ إِنَّ حِزۡبَ ٱللَّهِ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ
[ المجادلة : ٢٢ ]
ማስረጃው ተከታዩ የአሏህﷻ ንግግር ነው ፡- በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፡፡ ከእርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል፡፡ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፡፡ አላህ ከእነርሱ ወዷል፡፡ ከእርሱም ወደዋል፡፡ እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ንቁ! የአላህ ሕዝቦቸ እነርሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡
የአሏህን መልዕክተኛﷺ እወዳለሁ፣ እከተላለሁ፣ ትዕዛዛቸውን እፈፅማለሁ ክልከላቸውን እከለከላለሁ ለሚል አካል አጋሪዎችን ካህዲያኖችን፣ እንዲሁም የባጢል ባለቤቶችን ወዳጅ አድርጎ ሊይዛቸው አይፈቀድለትም።
ይህ ክፍል አምልኮን ፍፁም ለአሏህ ያጠራ ሲሆን የሚፈፅም አንድ አማኝ (ሙወሒድ) ካህዲያንን በፍፁም መወዳጀት እንደሌለበት ይገልፃል። አሏህﷻ የአማኝ ባህሪ ምን መሆን እንዳለበት ሲያወሳ አሏህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩ፣ የሚያስተባብሉ አካላቶችን በፍፁም ወዳጅ ሆኖ እንደማይገኝ ገለፀ።
https://t.me/AbumusabHassen
1226
14:27
23.08.2025
ሶስቱ መሠረቶች (الأصول الثلاثة )
ክፍል ሁለት
قَالَ الشَّافِعيُّ ـ رَحِمَهُ اللهُ تَعَالَى – : لَوْ مَا أَنْزَلَ اللهُ حُجَّةً عَلَى خَلْقِهِ إِلا هَذِهِ السُّورَةَ لَكَفَتْهُمْ
ኢማም አል ሻፍዕይ ረሂመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ “አሏህ በፍጡራኖቹ ላይ ከዚህች ሱራ ውጭ ማስረጃን ባያወርድ ኖሮ ትበቃቸው ነበር።”
እኒህ ታላቅ ኢማም አቡ አብዲላህ ሙሀመድ ኢብኑ ኢድሪስ ይባላሉ በ150 ዓ - ሂ ተወልደው በ204 ዓ - ሂ ሞቱ አሏህ ይዘንላቸው።
ከዚህ ከኢማሙ ሻፍዕይ ንግግር የሚፈለገው ይህች ሱራ የቁርዐንን ትዕዛዝ ጠቅልላ ይዛለች ማለት አይደለም። ነገር ግን ይህች ሱራ ብቻዋን ፍጡራን ሁሉ ያውቁ፣ ይተገብሩ፣ ጥሪ ያደርጉ እና ይታገሱ እንዲሁም ያስተነትኑ ዘንድ በቂ ማሰረጃ ነች ማለት ነው።
وَقَالَ البُخَارِيُّ ـ رَحِمَهُ اللهُ تَعَالَى ـ : بَابُ: العِلْمُ قَبْلَ القَوْلِ وَالْعَمَلِ؛
ኢማም አል ቡኻርይ ረሂመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ “ባብ እውቀት ከንግግርና ከተግባር በፊት ነው።
وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى:
فَٱعۡلَمۡ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ وَٱسۡتَغۡفِرۡ لِذَنۢبِكَ
[ محمد : ١٩ ]
ማስረጃው ተከታዩ የአሏህﷻ ንግግር ነው ፡- እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ምሕረትን ለምን፡፡
فَبَدَأَ بِالْعِلْمِ (قَبْلَ القَوْلِ وَالعَمَلِ )
በእውቀት ጀመረ (ከንግግርና ከስራ በፊት)
እኒህ ታላቅ የሙሀዲሶች መሪ (ኢማም) አቡ አብዲላህ ሙሀመድ ኢብኑ ኢስማኢል ይባላሉ በ194 ዓ - ሂ ተወልደው በ256 ዓ - ሂ ሞቱ አሏህ ይዘንላቸው። ከቁርዐን በመቀጠል ሙስሊሞች ሁሉ ማስረጃ አድርገው የሚጠቀሙበት ሶኺኽ አል ቡኻርይ የተሰኘው የሀዲስ ኪታብ ሰብሳቢ ናቸው።
ኢማም አል ቡኻርይ የእውቀትን ትሩፋትና የእውቀትን ልቅና እንገነዘብ እንዲሁም በትክክል እንረዳ ዘንድ እጥር ባሉ ጠቃሚ ቃላቶች ታላቅ ጭብጥን አስረድተዋል። እውቀት ከሁሉም ተቀዳሚው ስለመሆኑ ሲነግሩን ከንግግርም ከተግባርም እውቀትን አስቀደመ አሉ።
اعْلَمْ رَحِمَكَ اللهُ أَنَّه يَجِبُ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ وَمُسْلِمَةٍ، تَعَلُّمُ هَذِهِ المَسَائِل الثَّلاثِ ، والْعَمَلُ بِهِنَّ:
እወቅ አሏህ ይዘንልህና እነሆ እነዚህን ሶስት ነጥቦች አውቆ በእነሱ መስራት በሁሉም ሙስሊም ወንዶችና ሴቶች ላይ ግዴታ ነው።
ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ዓብዱል ወሃብ ረሂመሁሏህ እውቀት ፈላጊ ለሆኑ ወንድና ሴት አማንያን ሁሉ ማወቅ (መማር) በተማሩትም መስራት ግዴታ ይሆንባቸዋል ያሉትን ሶስት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ነጥቦችን በዚህ ንግግራቸው አወሱ።
الأُولَى:أَنَّ اللهَ خَلَقَنَا، وَرَزَقَنَا، وَلَمْ يَتْرُكْنَا هَمَلًا، بَلْ أَرْسَلَ إِلَيْنَا رَسُولًا، فَمَنْ أَطَاعَهُ دَخَلَ الجَنَّةَ، وَمَنْ عَصَاهُ دَخَلَ النَّارَ، ▪ የመጀመሪያው ነጥብ አሏህ እኛን ፈጠረን፣ ሲሳይንም ለገሰን። በከንቱም አልተወንም በል እንዴውም መልዕክተኛን ላከልን። እሱን የታዘዘ ጀነት ገባ እሱን ያመፀ (ያስተባበለ) ጀሀነም ገባ።وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى: إِنَّآ أَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡكُمۡ رَسُولٗا شَٰهِدًا عَلَيۡكُمۡ كَمَآ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ رَسُولٗا فَعَصَىٰ فِرۡعَوۡنُ ٱلرَّسُولَ فَأَخَذۡنَٰهُ أَخۡذٗا وَبِيلٗا [ المزمل : ١٥ ] ማስረጃው ተከታዩ የአሏህﷻ ንግግር ነው ፡- እኛ በእናንተ ላይ መስካሪ መልክተኛን ወደእናንተ ላክን፡፡ ወደ ፈርዖን መልክተኛን እንደላክን፡፡ ፈርዖንም መልክተኛውን አመጸ፤ ብርቱ መያዝንም ያዝነው፡፡ አሏህﷻ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ንግስና ሁሉ በእጁ ሲሆን፣ የሁሉም ነገር አስተናባሪ እንዲሁም ለፍጥረታቱ እርዚቅን ሲሳያቸውን ለጋስ የሆነ ብቸኛ አምላክ መሆኑን ማመን። እሱም በተውሒድ አር ሩቡብያህ ሊነጠል የሚገባው ብቸኛ ጌታ መሆኑን ማወቅና ማረጋገጥ ነው። አሏህ ፍጥረታትን ሁሉ ያስገኘው እሱ ሲሆን ፈጥሮ ልቅ አድርጎም አልተዋቸውም። ወደ ህዝቦች ሁሉ የሚያዛቸውና የሚከለክላቸው ሲሆን መልዕክተኛን ልኳል። መልዕክተኞችን የታዘዘ በእርግጥ አሏህን ታዟል መልዕክተኞችን ያስተባበለ አሏህን አስተባብሏል።
الثَّانِيَةُ: أَنَّ الله لا يَرْضَى أَنْ يُشْرَكَ مَعَهُ أَحَدٌ فِي عِبَادَتِهِ، لا مَلَكٌ مُقَرَّبٌ، وَلا نَبِيٌّ مُرْسَلٌ ▪ ሁለተኛው ነጥብ አሏህ ከእሱ ጋር አንድም አካል በአምልኮ ላይ ተጋሪ እንዲደረግበት አይፈልግም። የቅርብ ባለሟል መላኢካም ሆነ የተላከ ነብይ ቢሆን እንኳን።وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى: وَأَنَّ ٱلۡمَسَٰجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدۡعُواْ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدٗا [ الجن : ٨ ] ማስረጃው ተከታዩ የአሏህﷻ ንግግር ነው ፡- እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ (በውስጣቸው) ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ። ኢባዳ (አምልኮ) ሁሉ ለአሏህﷻ ብቻ የተገባ ነው። እርሱ አሏህ በተውሒድ አል ኡሉሂያህ ሊነጠል የሚገባው ብቸኛ ሀያል አምላክ ሲሆን ለእሱ በሚደረግ ኢባዳ ላይ ተጋሪን አካል አይፈልግም። ስግደት፣ ተማፅኖ (ዱአ)፣ እርድ፣ ስለት፣ ሸፈአ፣ በአደጋ ወቅት እርዳታን፣ ከአስፈሪ ነገሮች መጠበቅ እና በመሳሰሉ የኢባዳ ክፍሎች ተጋሪን አካል አይወድም። የቅርብ ባለሟል ከሚባሉ መላኢካዎችም ሆነ ከተላኩ ነብያት ቢሆን እንኳን አንድንም አካል በኢባዳ ላይ ተጋሪ እንዲደረግበት አይፈቅድም። ከአሏህ ውጭ አምልኮን መስጠት ሽርክ በእሱ ማጋራት ነው።
الثَّالِثَةُ: أَنَّ مَنْ أَطَاعَ الرَّسُولَ، وَوَحَّدَ اللهَ لا يَجُوزُ لَهُ مُوَالاةُ مَنْ حَادَّ اللهَ وَرَسُولَهُ، وَلَوْ كَانَ أَقْرَبَ قَرِيبٍ؛ ▪ ሶስተኛው ነጥብ መልዕክተኛውን የሚታዘዝ (የሚከተል) አሏህን በብቸኝነት የሚገዛ አካል። አሏህንና መልክተኛውን የሚከራከሩ ሰዎችን መወዳጀት አይፈቀድለትም። የቅርብ ቅርብ ዘመድ ቢሆኑም እንኳን።وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى: لَّا تَجِدُ قَوۡمٗا يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ يُوَآدُّونَ مَنۡ حَآدَّ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَوۡ كَانُوٓاْ ءَابَآءَهُمۡ أَوۡ أَبۡنَآءَهُمۡ أَوۡ إِخۡوَٰنَهُمۡ أَوۡ عَشِيرَتَهُمۡۚ أُوْلَٰٓئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلۡإِيمَٰنَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٖ مِّنۡهُۖ وَيُدۡخِلُهُمۡ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ رَضِيَ ٱللَّهُ عَنۡهُمۡ وَرَضُواْ عَنۡهُۚ أُوْلَٰٓئِكَ حِزۡبُ ٱللَّهِۚ
1126
14:27
23.08.2025
ሶስቱ መሠረቶች (الأصول الثلاثة )
ክፍል ሶስት
اِعْلَمْ أَرْشَدَكَ اللهُ لِطَاعَتِهِ، أَنَّ الْحَنِيفِيَّةَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ: أَنْ تَعْبُدَ اللهَ وَحْدَهُ، مُخْلِصًا لَهُ الدِّينَ. وَبِذَلِكَ أَمَرَ اللهُ جَمِيعَ النَّاسِ، وَخَلَقَهُمْ لَهَا؛
እወቅ አሏህ ቅኑን መንገድ ይምራህና እርሱን ለመታዘዝ። (አሏህ ለታዛዥነቱ ቀናውን መንገድ ይምራህና ) ሐኒፊያ ማለት የኢብራሂም መንገድ ነች። አሏህን ብቸኛ አድርገህ ልታመልከው ነው ሀይማኖትን (ዲንን) ለእርሱ ጥርት እና ፍፁም አድርገህ። በዚህ ላይ አሏህ የሰው ልጆችን በሙሉ ያዘዘና የፈጠረበት አላማ ነው።
كَمَا قَالَ تَعَالَى:
وَمَا خَلَقۡتُ ٱلۡجِنَّ وَٱلۡإِنسَ إِلَّا لِيَعۡبُدُونِ
[ الذاريات : ٥٦ ]
አሏህﷻ በተከበረ ቃሉ እንዳለው፦ ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
ሐኒፊያ ማለት ከሽርክ ጎዳና ወደ ተውሒድ ጎዳና መዘንበል ማለት ሲሆን። ሐኒፊያ ሲገለፅ በአሏህﷻ ከማጋራት ከሽርክ መንገድ በመውጣት ወደ ዲነል ኢስላም፣ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ወደ ተውሒድ መንገድ መዘንበል ነው። እሱም ለሽርክ ጀርባን በመስጠት አሏህን ብቻ በማምለክ ጎዳና ላይ ቀጥ ብሎ መጓዝ ማለት ነው።
ثُمَّ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ أَنِ ٱتَّبِعۡ مِلَّةَ إِبۡرَٰهِيمَ حَنِيفٗاۖ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
[ النحل : ١٢٣ ]
ከዚያም ወደ አንተ የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል፤ ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለት አወረድን፡፡
وَمَعْنَى يَعْبُدُونِ : يُوَحِّدُونِ، وَأَعْظَمُ مَا أَمَرَ اللهُ بِهِ التَّوْحيِدُ، وَهُوَ: إِفْرَادُ اللهِ بِالْعِبَادَةِ. وَأَعْظَمُ مَا نَهَى عَنْه الشِّركُ، وَهُوَ: دَعْوَةُ غَيْرِهِ مَعَهُ،
ሊያመልኩኝ (ሊገዙኝ) ማለት ትርጉሙ አንድና (ብቸኛ ቢጤ የለሽ) ሊያደርጉኝ ማለት ነው። አሏህ ካዘዘን ትልቁ ነገር ተውሒድ ነው። እሱም ተውሒድ ማለት አሏህን በኢባዳ መነጠል ማለት ነው። ከከለከለው ትልቁ ነገር ሽርክ ነው። እሱም ሽርክ ማለት ከአሏህ ጋር ሌላን አካል መጣራት ነው።
وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى
وَٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُشۡرِكُواْ بِهِۦ شَيۡـٔٗاۖ
[ النساء : ٣٦ ]
ማስረጃው ተከታዩ የአሏህﷻ ንግግር ነው ፡- አላህንም ተገዙ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡
▣ አሏህﷻ ካዘዘን ትልቁ ትዕዛዝ ተውሒድ ነው። ተውሒድ ማለት በቋንቋ ደረጃ አንድን ነገር ብቸኛ ማድረግ መነጠል ማለት ሲሆን በኢስላም እይታ አሏህን ብቸኛ ማድረግ ማለት ነው። ይህም አሏህንﷻ በፈጣሪነቱ፣ (ተውሒድ አር ሩቡብያህ) በተመላኪነቱ፣ (ተውሒድ አል ኡሉሂያህ) በስምና ባህሪያቱ (ተውሒድ አል-አስማ ወስ-ሲፋት) መነጠል ማለት ነው።➲አሏህንﷻ በጌትነቱ መነጠል (ተውሒድ አር ሩቡብያህ) አሏህﷻ በፈጣሪነቱ፣ በአስተናባሪነቱ፣ በንግስናው አንድና ብቸኛ ነው። የሰማያት፣ የምድር፣ እንዲሁም በመካከላቸውና በውስጣቸው ሁሉ ያሉትን የፈጠረ አለማትን ያለ ረዳት ያስገኘ ሀያል አምላክ ነው። መጠኑንም አስተካከለው፣ መራውም ከፍጡራን መካከልም አንድም በሰማያት ወይም በምድር ያለን ቅንጣት ነገር ፈጥሪያለሁ ሊል አይገባውም። ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖۖ [ الزمر : ٦٢ ] አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ ➲አሏህንﷻ በአምላክነቱ መነጠል (ተውሒድ አል ኡሉሂያህ) አሏህﷻ ብቸኛ ተመላኪ ሲሆን በአምላክነቱ አንድ ነው። ከእሱ ሌላ በፍርሃት እና በተስፋ የሚያድሩለት፣ የሚተናነሱለት፣ እዝነቱን የሚከጅሉት፣ ትእዛዙንም ያለ ተቃውሞ የሚፈጽሙለት፣ የሚመኩበት አንድም የለም። ሁሉም ነገር ለእርሱ ብቻ ነው። አሏህﷻ ሁሉን ነገር የፈጠረ ሲሆን ለአምልኮም የተገባ አምላክ ነው። وَإِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ [ البقرة : ١٦٣ ] አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ መላኢካዎች፣ ነብያት፣ የአሏህ ወዳጆች (ወልዮች)፣ ንጉሶች እና ባለስልጣናት ሁሉም የአሏህ ባሮች ሲሆኑ በአሏህ አሸናፊነት ስር ናቸው። መጥቀምም ሆነ መጉዳት፣ ሕይወት መስጠትም ሆነ መንሳት አይችሉም። ስለዚህ ኢባዳ (አምልኮ) አይገባቸውም። ጉዳት የመገፍተርና ጥቅምን የማምጣት ባለቤት አሏህﷻ ብቻ ነው። ኢባዳ አምልኮ ለአሏህ በቻ ነው። ➲አሏህንﷻ በመልካም ስምና ባህሪው መነጠል (ተውሒድ አል-አስማ ወስ-ሲፋት) አሏህﷻ በምሉዕ ስምና ባህሪያት የሚገለፅ፣ ከጎደሎ ባህሪያት ሁሉ የጠራ፣ በመልካም ስሞች የሚጠራ የአለማት ፈጣሪ ሀያል አምላክ ነው። አሏህንﷻ ከፍጡራን የሚመስለው አንድም የለም። አሏህﷻ ከፍጥረታቱ ሁሉ የተለየና ቢጤ የለሽ ነው። ለአሏህﷻ ስምና ባህሪያትን ሲያፀድቁ በቁርዐንና በሱና የተገለጹ የአሏህን ስሞችና ባህሪያት ትርጉማቸውን ሳይለውጡ (ተሕሪፍ)፣ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ ሳያደርጉ (ተዕጢል)፣ በምናብ ቅርፅ ሳያስይዙ (ተክይፍ) ወይም ከፍጡራን ባህሪያት ጋር ሳያመሳስሉ (ተሽቢህ) በሙሉ ልብ አምኖ መቀበል ነው። لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ [ الشورى : ١١ ] የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡
▣ አሏህﷻ ከከለከለን ትልቁ ክልከላ ሽርክ ነው። ሽርክ ማለት አሏህﷻ ሊነጠልበት ሲገባው ለእሱ በሚገቡ ነገራቶች ሁሉ ተጋሪን፣ ባላንጣንና ቢጤን ማድረግ ነው። ይህም በአሏህﷻ ጌትነት በፈጣሪነቱ (ተውሒድ አር ሩቡብያህ) እንዲሁም በአምልኮ (ተውሒድ አል ኡሉሂያህ) በስምና ባህሪያቱ (ተውሒድ አል-አስማ ወስ-ሲፋት) ሌላን አካል ተጋሪ ቢጤ ማድረግ ነው።የመካ አጋሪያን ይተገብሩት የነበረው የሽርክ አይነት በተውሒድ አል ኡሉሂያህ በአምልኮ ላይ ሌላን አካል በማጋራት ነበር። ሽርክ ሲወሳ የሚያስረዳውም ለአሏህ በሚደረግ አምልኮ ከአሏህ ጋር ሌላን አካል ተጋሪ፣ ባላንጣ፣ ሸሪካ ማድረግ ነዉ። ሽርክ የኢባዳ አይነቶችን ለመላኢካ፣ ለነብያት እና ለሷሊሆች በማዋል ይፈፀማል። ምሳሌ፡- ስለት፣ እርድ፣ ዱአ፣ ጭንቅ በሚገጥማቸዉ ጊዜ በቀብር ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ፣ ከአሏህ ዉጭ ማንም መፈፀም የማይችለዉን ጉዳይ ከሙታኖች የይድረሱልኝ ጥሪ በማድረግ (ኢስቲጛሳ) እና በመሳሰሉ የአምልኮ አይነቶች ከአሏህ ዉጭ በመስጠትና በማዋል የሽርክ ተግባር ይገኛል፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَغۡفِرُ أَن يُشۡرَكَ بِهِۦ وَيَغۡفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَآءُۚ [ النساء : ٤٨ ] አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ إِنَّهُۥ مَن يُشۡرِكۡ بِٱللَّهِ فَقَدۡ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِ ٱلۡجَنَّةَ وَمَأۡوَىٰهُ ٱلنَّارُۖ [ المائدة : ٧٢ ] እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡
https://t.me/AbumusabHassen
1259
20:11
23.08.2025
የአባቶችህ እምነት የነብያቶች፣ የሲዲቆች፣ የሷሊሆች የአሏህ ወዳጆች መንገድ። ከሽርክ የራቀ የተውሒድ እምነት። ከቢድአ የጠራ የሱና ጎዳና እስልምና ሆኖ ካገኘኸው ተከተለው።
https://t.me/al_burhann
890
20:30
23.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
ቁርአን 🌷መልካም አዳር 🫀
187
23:19
23.08.2025
imageImage preview is unavailable
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
ርዕስ፦»»» በደረጃ «««
✎ ፀሐፊ፦ Abdulkarim 🇵🇸
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
በ Abdulkarim 🇵🇸 የተዘጋጀ
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
አዲስ ተከታታይ ታሪክ የትም ያልተነበበ ማክሰኞ ይጀምራል እስከዛ ተቀላቀሉን👇
🥀በደረጃ🥀 የሚለውን Click አርጉት💞
5
16:59
24.08.2025
imageImage preview is unavailable
ለባለቤትህ(ለሚስትህ) #ምርጥ_ሁን።
ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ከእናንተ መካከል ምርጥ ሰው ማለት ለሚስቱ ምርጥ የሆነ ሰው ነው። እኔ ለሚስቶቼ ከእናንተ የበለጠ ምርጥ ነኝ።"
📚ቲርሚዚ ዘግበውታል📚
🌹🍃ـ 🌹🍃ـ
0
17:52
24.08.2025
ሶስቱ መሠረቶች (الأصول الثلاثة )
ክፍል አራት
فَإِذَا قِيلَ لَكَ: مَا الأُصُولُ الثَّلاثَةُ التِي يَجِبُ عَلَى الإِنْسَانِ مَعْرِفَتُهَا؟ የሰው ልጅ ሊያውቃቸው ግዴታ የሚሆኑበት ሶስቱ መሠረቶች ምን ምን ናቸው በተባልክ ጊዜ?
فَقُلْ: مَعْرِفَةُ الْعَبْدِ رَبَّهُ، وَدِينَهُ، وَنَبِيَّهُ مُحَمَّدًا صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ. አንድ ባሪያ ጌታውን ማወቅ፣ ሃይማኖቱን ማወቅ፣ እንዲሁም መልዕክተኛውን ሙሐመድ ﷺ ማወቅ ነው፡፡ ብለህ መልስ።ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ዓብዱል ወሃብ ረሂመሁሏህ የሰው ልጆች ሁሉ ሊያውቋቸው ግዴታ የሆኑባቸውን ሶስት መሠረቶች ምን ምን ናቸው የሚለውን ጥያቄ ከመልስ ጋር አስቀመጡ። እነሱም አንድ ባሪያ ጌታውን ማወቅ፣ ሃይማኖቱን ማወቅ እንዲሁም መልዕክተኛውን ሙሐመድ ﷺ ማወቅ የሚሉ ናቸው። ለዚህም ነው ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ዓብዱል ወሃብ ቁርዐን ሀዲስን መሠረት አድርገው ኡሱሉ ሰላሳ በማለት ሪሳላቸውን የፃፉት።
● الأَصْلُ الأَوَّلُ مَعْرِفَةُ الرَّبِّ ●➤ የመጀመሪያው መሠረት ጌታህን ማወቅ ነውሸይኽ ሙሀመድ ቢን ዓብዱል ወሃብ ረሂመሁሏህ የሰው ልጅ ማወቅ ከሚገባው ሶስት መሠረቶች ውስጥ የመጀመሪያውን መሠረት አስቀመጡ። እሱም አንድ ሰው መጀመሪያ ማወቅ የሚገባው የፈጠረውን ፈጣሪ አሏህንﷻ ማወቅ ነው። የተፈጠርንለትን አላማ ጠንቅቆ ማወቅ በሳል መሆን ነው። የሰው ልጅ የተፈጠረው ሊበላ፣ ሊጠጣ እንደፈለገ ሊፈነጥዝ አይደለም። የሰውን ልጅ አሏህ ለከንቱ አላማ አልፈጠረውም። እርሱን እንዲገዙት ቢሆን እንጅ። فَإِذَا قِيلَ لَكَ: مَنْ رَبُّكَ؟ ጌታህ ማንነው ተብለህ በተጠየቅክ ጊዜ? فَقُلْ: رَبِّيَ اللهُ الَّذِي رَبَّانِي، وَرَبَّى جَمِيعَ الْعَالَمِينَ بِنِعَمِهِ، وَهُوَ مَعْبُودِي لَيْسَ لِي مَعْبُودٌ سِوَاهُ؛ ብለህ መልስ፦ ጌታየ አሏህ ነው። ያ ጌታ እኔንም ሆነ መላ ፍጥረተ ዓለሙን በአጠቃላይ በችሮታው (በፀጋው) የሚንከባከብ የሆነው፡፡ እርሱም በብቸኝነት የማመልከው ነው። ከእርሱ ውጭ ሌላ የማመልከው የለኝም፡፡ وَكُلُّ مَنْ سِوَى اللهِ عَالَمٌ، وَأَنَا وَاحِدٌ مِنْ ذَلِكَ الْعَالَمِ. ከአሏህ ውጭ ያለው ሁሉም አለም ነው። እኔ ደግሞ ከዚህ አለም ውስጥ አንዱ ነኝ። وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ [ الفاتحة : ٢ ] ማስረጃው ተከታዩ የአሏህﷻ ንግግር ነው፡- ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤ فَإِذَا قِيلَ لَكَ: بِمَ عَرَفْتَ رَبَّكَ؟ ጌታህን በምን አወቅከው ተብለህ በተጠየቅክ ጊዜ? فَقُلْ: بِآيَاتِهِ وَمَخْلُوقَاتِهِ، وَمِنْ آيَاتِهِ: اللَّيْلُ، وَالنَّهَارُ، وَالشَّمْسُ، وَالْقَمَرُ، وَمِنْ مَخْلُوقَاتِهِ السَّمَاوَاتُ السَّبْعُ وَالأَرَضُونَ السَّبْعُ وَمَنْ فِيهِنَّ، وَمَا بَيْنَهُمَا؛ ጌታየን ያወቅኩት በተዓምራቱ (በምልክቶቹ) እንዲሁም በፍጥረታቱ ነው ብለህ መልስ። ከተዓምራቶቹ መካከል ለሊትና ቀን፣ ፀሐይ እና ጨረቃ ፤ ከፍጥረታቶቹ መካከል ደግሞ ሰባት ሰማያት እና ሰባት ምድሮች በውስጣቸው እንዲሁም በመካከላቸውም ያሉት ናቸው፡፡ وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى وَمِنۡ ءَايَٰتِهِ ٱلَّيۡلُ وَٱلنَّهَارُ وَٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُۚ لَا تَسۡجُدُواْ لِلشَّمۡسِ وَلَا لِلۡقَمَرِ وَٱسۡجُدُواْۤ لِلَّهِۤ ٱلَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمۡ إِيَّاهُ تَعۡبُدُونَ [ فصلت : ٣٧ ] ማስረጃው ተከታዩ የአሏህﷻ ንግግር ነው፡- ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደ ኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)፡፡ وَقَوْلُهُ تَعَالَى: إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يُغۡشِي ٱلَّيۡلَ ٱلنَّهَارَ يَطۡلُبُهُۥ حَثِيثٗا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ وَٱلنُّجُومَ مُسَخَّرَٰتِۭ بِأَمۡرِهِۦٓۗ أَلَا لَهُ ٱلۡخَلۡقُ وَٱلۡأَمۡرُۗ تَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ [ الأعراف : ٥٤ ] ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም (ለክብሩ በሚስማማ መልኩ) በዐርሹ ላይ ከፍ አለ። (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ የሚፈልገው ሲኾን ይሸፍናል፡፡ ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)፡፡ ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡ وَالرَّبُ هُوَ الْمَعْبُودُ، ፈጣሪ (ረብ) ማለት እርሱ ተመላኪው ነው። አሏህﷻ ካለመኖር ወደ መኖር አመጣን። አስተካክሎም ፈጠረን። ይህ የሆነው ያለ አላማ አይደለም። እርሱን ብቻ በብቸኝነት እንድንገዛው ነው። وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى: يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱعۡبُدُواْ رَبَّكُمُ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ فِرَٰشٗا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءٗ وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجَ بِهِۦ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ رِزۡقٗا لَّكُمۡۖ فَلَا تَجۡعَلُواْ لِلَّهِ أَندَادٗا وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ [ البقرة : ٢٢-٢١ ] ማስረጃው ተከታዩ የአሏህﷻ ንግግር ነው፡- እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ (እርሱ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው፤ ከሰማይም (ከደመና) ውሃን ያወረደ በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው፡፡ እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ፡፡
አሏህﷻ የሰውን ልጅ የፈጠረው እርሱን ብቻ በብቸኝነት እንዲገዙት እንዲያመልኩት ነው። ለዚህም ነው አሏህﷻ በተከበረ ቃሉ እርሱን ብቻ እንድናመልከው እኛን በመፍጠሩ ማስረጃ ያደረገው።قَالَ ابْنُ كَثِيرٍ ـ رَحِمَهُ اللهُ تَعَالَى : الخَالِقُ لِهَذِهِ الأَشْيَاءَ هُوَ الْمُسْتَحِقُّ لِلْعِبَادَةِ. ኢብኑ ከሲር ረሂመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ እነዚህን ነገራቶች (ከላይ በቁርዐን አያው የተጠቀሱትን) የፈጠረ ፈጣሪ እርሱ ለኢባዳ ለአምልኮ የተገባ ነው።
https://t.me/AbumusabHassen
1261
17:20
24.08.2025
ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ رضي الله عنه ጀናዛውን መላዒካዎች የተሸከሙት እና ዓርሽ የተንቀጠቀጠለት ሰሃባ በእስልምና ውስጥ የቆየው 7 ዓመታትን ብቻ ነበር። እኛ ስንት ዓመታትን ቆይተን ልባችን አለመርጠቡ ያማል።
@heppymuslim29
594
21:41
25.08.2025
close
Reviews channel
No reviews
Channel statistics
Rating
7.1
Rating reviews
0.0
Сhannel Rating
0
Subscribers:
1.0K
APV
lock_outline
ER
--%
Posts per day:
3.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий