
Get clients in any niche!
Delegate the launch of advertising to us — for free
Learn more
6.3

Advertising on the Telegram channel «አብርሆት ቤተ መጻሕፍት- Abrhot Library»
Books, Audiobooks & Podcasts
Language:
Amharic
50
0
#አብርሆት
📖 እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ እዚህ ቻናል ላይ መፅሀፍትን በፒዲኤፍ እና የተለያዩ ትረካዎችን ያገኛሉ።
📚 "መፅሀፍት ሁሌም እንደ አዲስ የምንከፍታቸው የህይወት ዘመን ስጦታዎች ናቸው።"
✏️ ጋሪሰን ኬይለር
🚧 ቻናላችንን ሼር በማድረግ አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት ያግዙ
📚📚📚📚📚📚
📚 #ንባብ 📚
Share
Add to favorite
Channel temporarily not accepting requests
Choose another channel from recommendations or get a tailored list within your budget using AI
AI Channel Picker
Recent Channel Posts
ይህው መጽሐፉ አንብቡት!
ውልብታ - አለማየሁ ገላጋይ
📚 @metsehaf
1700
21:41
24.07.2023
ብንን ስል እናቴ እጆቿን አጣጥፋ ተቀምጣለች።እራት አልነበረም ቁርስም አይኖርም እያለች መሰለኝ
"ህልም አየሁ" አልኳት
አንተን ብሎ ባለህልም፣ፈሳም አለችኝ
"እትዬ ደጅ ይጥኑ እንጀራ በሰፌድ አድርገው ሲሰጡኝ ብንን አልኩኝ"
ትንሽ ብትቆይ ወጥ አድርገውልህ ልትበላ አነበር? ምን አስቸኮለህ?
የቁርስ አለመኖር ችግሯን በእኔ ህልም ልታሳብብ እየከጀላት መሰለኝ።
"በል ሂድና ይሄንኑ ህልም ለእሳቸው ንገራቸው።ነገር ግን ህልሙን እንዳየህው ሳይሆን ልጅዎት ልኮኝ እንጀራ በሰፌድ አምጥቼ ሰጠሁዎት በላቸው።"
ህልም ይስተካከላል? ወይስ እንደታየ ይነገራል?
እትዬ ደጅ ይጥኑ ደጃፍ ደረስኩ።እንጀራ እየጋገሩ ነበር።ቅመም ያለው ሻይ አፍንጫዬ ላይ ወረራ አካሄደ።ህልም እንዳየው ስነግራቸው ልክ እንደ እናቴ፦
"አንተን ብሎ ባለህልም፣ፈሳም" አሉኝ።
እናቴ እንዳስተካከለችው አድርጌ ህልሜን ነገርኳቸው።
"ትልልቆቹ ቢሆኑ ደስ አይበላት ብለው አይነግሩኝም ነበር።አቤት ሲሳይ፣አቤት ሲሳይ፣የትኛው ልጄ? እያሉ ህልሙን አስደጋገሙኝ።ትኩስ እንጀራ ከትኩስ ሻይ ጋር ሰጡኝ።የተጣበቀውን ትኩስ እንጀራ ስቆርስ የእርቦው ስፌት በጥፍሬ እየተቃኘ እርካታዬን አጀበልኝ።ወደቤት ስመለስ እናቴ ድምጿን ከፍ አድርጋ እየተሳደበች ገረፈችኝ።
"እዚህ የሰራሁልህን ቁርስ ዘርግተህ ጥለህ ሄድክ? አፈር ብላና....
📓 ውልብታ
✍🏻 አለማየሁ ገላጋይ
📚 @metsehaf
1600
21:41
24.07.2023
ሁሉም ነገር ትክክል ነበር። ህይወቴ ፀፀት አልባ ነበር ። እራሴ ነበርኩ የመስመሬ ቀያሽ ። አያያዝህ ያስታውቃል ጥሩ ላይ ነህ የማይለኝ አልነበረም ለመጥበስ አጀናጀኔ ፤ አፈላለጌ አበላለጌ ክብሬን የመጠነ ነበር።
ድንገት አንዲት ጠይም ሰውነታም ፤ቅልስልስ ወደ ህይወቴ መጣች ። ተግባባን
በጋራ ሻይ መጠጣት ቢራ መጎንጫጨት ጀመርን ።
ታደንቀኛለች ለኔ ያላትን መልካም ቦታ በየአጋጣሚው ሹክ ትለኛለች ። ጉረኛነት እና ትህትና እንዴት አብሮ ሄደልክ ትለኛለች በስሱ እየሳቀች ።
እግሬን ሳላነባብር ከወገቤ ለጠጥ ሳልል መቀመጥ አለመቻሌን እያየች ፈገግ ትላለች። ፈገግ ስትል አይኖ ጭፍን ይልና ዲንፕሏ ይሰረጉዳል ።
በትንሹ ትሳፈጠኛለች ያላየሁትን ቦታ እና ሁኔታ ታሳየኛለች። ካጠፋች እቆጣታለሁ ደግሜ አላጠፋም ብላ ይቅርታ ትለኛለች
ከንፈሬን በገሚስ ትስመኛለች እየተቆጣዋት እንደነበር ዘንግቼ ሙሉ ከንፈሬ እንዲሳም ከንፈሬን አመቻችላታለሁ ። ትስቃለች ሳቋ የተኮሳተረውን ፊቴን ይፈግገዋል ።
ሳላገኛት የማድረበት ቀን ጥቂት ነው ።
አመስጋኝነቷን ደስስ ይለኛል። ሳትሞገት ሳይሰለቻት እኔ ነይ ያልኳት ቦታ ትገኛለች። ስለ ምንም ሳወራት አትኩራ በትህትና ትመለከታኛለች ።
ብዙ የሚጎረብጥ ነገር ታደርጋለች እንደበፊቱ ከመቆጣት መለማመጥ ጀመርኩ ።
በጠየኳት ግዜ የጠየኳትን ትሰጠኛለች ። ምቾቴን ትጠብቅልኛለች። እንዲ ኑሮዬን ኑሯዋ ፣ ጉዳዮን ጉዳዬ ካደረኩ ነፍፍ ግዜ ሆነ ።
ቀስስስ እያለች እኔ ጋ መምጣት አቆመች እኔ እሷ ጋ ሄድኩ፤ ቀስስ እያለች በየቀኑ መደወል አቆመች እኔ በየቀኑ መደወል ጀመርኩ ።
ቀስስ እያለች ያደረገችልኝን ሙሉ ለሙሉ እኔ ማድረግ ጀመርኩ ፤ እኔ ቀስ እያልኩ መነጫነጭ፤ ቀስ እያልኩ መቅናት ጀመርኩ ። ለኔ በብዙ መጠንቀቅ አቆመች ። ስታወራኝ እንደሚከፋኝ አይገባትም ። ድክመቴ ሆነች ።
ትላንት ባቆላመጠችኝ ልክ እንድታቆላምጠኝ ስጦታ ካቅሜ በላይ እገዛለሁ ቁልምጫዋ ውሎ አያድርም። በትላንት መጠን እንድትፈራኝ እጮኽባታለሁ ስጮኽባታ ታኮርፈኛለች፤ ስልኳን ታጠፋብኛለች መሄጃ አጣለሁ ሁሉ ነገር ጨው ጨው ይለኛል ትናፍቀኛለች ትኖርበታለች ያልኩት ስፍራ ሄጄ ይቅርታ እጠይቃታለሁ።
እራሴ ላይ አቅም አጣሁ ። እንዳልተዋት እወዳታለሁ። አብሬያት እንዳልሆን እልህ አለመፈለግ ተደራርቦ የፍቅሬን ተፈጥሮአዊ በሃሪ ነጥቆኛል ።
አብርያት ነኝ ። ከዚህ ድብልቅ ካለ ስሜት የሚያወጣኝ ሃይል አጥቻለሁ እንዳገባት ከፈለገች አገባታለሁ ። ተጋብተን የሚኖረን የሃይል አስተላለፍ ጌታ ያቃል ። ህይወት ድል ብቻ የምታጣጥምባት መንገድ አይደለችም ።
ማስታወሻ
ምቾትህ ባርያ እንዲያርግህ አትፍቀድለት 🙏
1300
16:15
24.07.2023
ፈላስፋ ቅዱስ ዮሃንስ እንዲ ይላል
“Why not learn to enjoy the little things-there are so many of them.”
ደስታ በስኬት ሳይሆን አለምን በተረዳንበት መንገድ የምናገኘው ቅመም ነው። life ለማንም ቀላል አይደለችም የሁሉም ሰው ህይወት ትግል ነው ልዩነቱ የትግሉ አይነት ነው።
ደስታ በልምምድ የሚመጣ ገፀ በረከት ነው ። ሁሉን ኖሮን ደስታ ከሌለን ያለን ከሌለን አይሻልም !!
ሃሌ ሉያ
ቡድሃም እንዲ አለ
“There is no Path to Happiness; Happiness is the Path.” ደስታን ማግኛ መንገድ የለም መንገዱ ራሱ ደስታ ነው እንደማለት አይደል ይሄ መንገድ ደሞ እይታ ነው ። እይታችን ነው የደስታችንን ብርሃን የሚያበራው ።
አብርሃም ሊንከን እንደሚለው In the end, it’s not the years in your life that count. It’s the life in your years.በመጨረሻ በህይወታችን ውስጥ የሚቆጠሩት ዓመታት አይደሉም። በአመታታችን ውስጥ ያለው ሕይወት እንጂ ።
ተሰፍሮ የተሰጠን ህይወት እንስክታልቅ ትንሽ እየተማረርን ፤ ትንሽ ተስፋ እየቆረጥን ትንሽ እየተናደድን ትንሽ እየተብከነከን በዙ በጣም ብዙ እንደሰታለን ፦
ሃሌ ሉያ 🙏
ደስታ ከኛ ጋ ትሁንልን ❤
1400
06:46
24.07.2023
play_circleVideo preview is unavailable
📚ርዕስ: "የጡት አባት ~ The Godfather"
📝ደራሲ: ከማርዮ ፑዞ (Mario Puzo)
👤ትርጉም: ወጋየሁ ተበጀ
📜ዘውግ: ልብ-ወለድ
📖የገጽ ብዛት: 559
📖ፍራንሲስ ፎርድ ኮፖላ መፅሀፉን ወደ ፊልም ሲቀይር ማፊያዎቹ ፊልሙ እንዴት እንደሚሰራ የሚሰልይ ሰላይ ላኩ። ለስለላ የተላከው ደግሞ የቀድሞ የነፃ ትግል ተጋጣሚ እና በፊልም ሳይሆን በእውኑ የማፊያዎች የወንጀል ግብረአበር ሌኒ ሞንታና ነው። ባለ ንስር አይኑ አዘጋጅ ኮፖላ ሌኒን በተደጋጋሚ ሲያየው አይኑ ውስጥ ገባ። ሉካ ብራዚ የተባለውን ምህረትየለሽ ማፊያ እንዲጫወት አጨው። ሁለቱም ግዙፍ ናቸው። ሁለቱም የማፊያ ግብረአበሮች ናቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ ሌኒ ሞንታና እየተወነ ሳይሆን ራሱን እየተጫወተ ነበር።
ሌላው ጉዳይ ሞንታና ከማርለን ብራንዶ ጋር መተወኑ አስፈርቶት ነበር። ብራንዶ በጣም ዝነኛ አክተር ነው። ሞንታና ከብራንዶ ጋር ሲገናኝ በጣም ነርቨስ ይሆን ነበር። ታድያ አዘጋጁ ኮፖላ ይህንን ፍርሃቱን የፊልሙ ስክሪፕቱ ውስጥ አስገብቶ የታሪኩ አካል አደረገው።
ወደ ሉካ ብራዚ ስንመጣ የታመነ የኮርሌዎኔ አገልጋይ ነበር። ቨርጂል ሶሎዞ የኮርሌዎኔ ጠላት ነው። ኮርሌዎኔ ሶሎዞን ለማንበርከክ ብራዚን መጠቀም ፈልጎ ይልከዋል። ይኼኔ ሶሎዞ ቀድሞ ነቅቶ ብራዚን ያስገድለዋል። ብራዚ ለብሶት የነበረውን የጥይት መከላከያ ልብስ ውስጥ የሞተ አሳ ሞልቶ ለኮርሌዎኔ ይልክለታል። መልእክቱ ግልፅ ነበር―ሉካ ብራዚ ከአሳዎቹ ጋር ተኝቷል/ሞቷል ማለት ነበር። ነፍስ ይማር!!!
https://t.me/+y28V2kexfVZjNzVk
2634
15:56
20.07.2023
imageImage preview is unavailable
፨ የጡት አባት ( The God father )
ለትርጉም መፅሐፍ ወዳጆች እነሆ ድንቅ በድርጊት የታጀበ ልብ ወለድ መፅሐፍ ::
መፅሐፍ የሚያትተው በድብቁ አለም የሚሰሩትን አስገራሚ የወንጀል ድርጊቶችን ሚስጥር እንዲሁም በዚህ የማፊያዎች የውድድር ሩጫ የሚደረጉ ድብቅ ሴራ እና አስገራሚ የቤተሰብ ፍቅር ::
የሚገርመው ይህ መፅሐፍ በቃና ቲቪ በሚተላለፈው* የኛ ሰፈር * የሚለው የቱርክ ድራማ ከዚሁ መፅሐፍ ላይ ተወስዶ የተሰራ ታዋቂ እና ተወዳጅ ድርሰት ነው ።
ለመጀመሪያ ጊዜ መፅሐፍ 1982 ተተረጎመ
ለመጨረሻ ጊዜ 2010 ተተርጉሞ ለአንባቢያን በቃ ።
ደራሲው : ማሪዮ ፑዞ
ትርጉም : ወጋየሁ ተበጀ
እኔ ወድጄዋለሁ እርሶም ይጋበዙልኝ ።
https://t.me/+y28V2kexfVZjNzVk
2195
15:56
20.07.2023
[👉 75 በመቶው የዓለም ምግብ የሚመረቱት ከ12 ዕፅዋትና ከአምስት የተለያዩ የእንስሳት ዝርያዎች ብቻ ነው።
👉 ኒትረስ ኦክሳይድ የተባለ ጋዝ አንዴ ካሸተትነው ሳንወድ በግዳችን እንድንስቅ ያረገናል ።
ይህ ኬሚካል ''ላፊንግ'' ጋዝ ተብሎ ይጠራል ።
👉 አፍሪካ ውስጥ ከ 40 ሰዎች አንዱ ብቻ ነው ስልክ ያለው
👉የቫዮሊን ገመዶች በተለምዶ ከፈረስ ፀጉር የተሠሩ ናቸው።](https://t.me/+y28V2kexfVZjNzVk)
2347
04:35
20.07.2023
imageImage preview is unavailable
[ከሮበርት ሙጋቤ ንግግር የቀጠለ .....
#Part_5
..... ምድር ላይ ያሉት ሴቶች በሙሉ የኤች አይቪ ኤድስ መድሀኒት እስካልተገኘ ድረስ ምንም አይነት የግብረስጋ ግንኙነት አናደርግም ብለው ቢያምፁ ኖሮ ... ይሄን ግዜ ወንዶች መድሀኒቱን በ 30 ቀን ውስጥ ባገኙት ነበር 😂
#ሮበርት_ሙጋቤ 😁👏](https://t.me/+y28V2kexfVZjNzVk)
2295
18:36
19.07.2023
play_circleVideo preview is unavailable
📚ርእስ 📕:-7 ቁጥር
📝ደራሲ 👤:-መስፍን ሰለሞን ሙሀባ
📆ዓ. ም :-2012
Password :-7
═════════════════
══
SHARE and JOIN🙏
@metsehaf
@metsehaf
781
21:51
01.07.2023
የ "7" ቁጥር ኮድ ክፍል 1
🚢🚢🚢🚢🚢
*7 ቁጥር የዓለም የምህንድስና፣የተፈጥሮ፣የሰው ልጅ ስሪት ኮድ ናት።ምሉዕ ናት።ፊዚክስ፣ባይሎጂው እና ተፈጥሮ ሳይንስ 7 ቁጥርን መሰረት ያደረጉ ናቸው።7 ቁጥር በተፈጥሮ ሳይንስ ምስጢራዊ ኮድ አላት።ለምሳሌ፦
🚢🚢🚢🚢🚢🚢
*የአፈር ዝርያዎች 7 ናቸው።እነርሱም፦
1.የእርሻ አፈር፣
2.የማዕድን አፈር፣
3.መንገደኛ አፈር፣
4.ቀዝቃዘው አፈር
5.የመድኃኒት አፈር
6.ስውሩ አፈር
7.ውሐ ተሸካሚ አፈር ናቸው።
🚢🚢🚢🚢🚢🚢
*መንገደኛ አፈር የሚባለው በአውሎፋስ የሚጓዘው ሲሆን ቀዝቃዛው አፈር የተፈጥሮን የአየር ሚዛን የሚጠብቅ ሙቀትን ከፀሐይ ተመግቦ ቀዝቃዜ አየር የሚተፋ ነው።ስውሩ አፈር የሰው ልጅ የተፈጠረበት አፈር ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ይገኛል።ለመድሃኒትነትም ይውላል።
🚢🚢🚢🚢🚢🚢
*ለሰው ልጅ አገልግሎት የሚውሉ የተፈጥሮ ሀብቶች 7 ናቸው።
1.ውኃ
2.አፈር
3.ማዕድናት
4.እጽዋት
5.የዱር እንስሳት
6.አየር
7.ወንዝ ናቸው።
🚢🚢🚢🚢🚢
*በዓለም ላይ 7 አኀጉሮች አሉ።እነርሱም፦
1.እስያ፣
2.አፍሪካ፣
3.ሰሜን አሜሪካ፣
4.ደቡብ አሜሪካ፣
5.አንታርክቲካ፣
6.አውሮፓ
7.አውስትራሊያ ናቸው።
🚢🚢🚢🚢🚢
*በዓለም 7 ውቅያኖሶች አሉ።
1.ህንድ ውቅያኖስ
2.አትላንቲክ ውቅያኖስ
3.ፓስፊክ ውቅያኖስ
4.አርስቴክ ውቅያኖስ
5.ሜዴትራሊያን ውቅያኖስ
6.ካሪቢያን ባህር
7.ሜክሲኮ ባህር ገብ ናቸው።
🚢🚢🚢🚢🚢
*በዓለም 7 ሞቃት በረሃዎች አሉ።እነርሱም ፦
1.ሰሐራ በረሃ
2.ጎቢ በረሃ
3.ታር በረሃ
4.አውስትራሊያ በረሃ
5.አታካማ በረሃ
6.አረቢያን በረሃ
7.ኮሌራዶ በረሃ ናቸው።
🚢🚢🚢🚢🚢
*የሰው ልጅ የሚመገባቸው የተፈጥሮ ዝርያዎች ሰባት ናቸው።እነርሱም፦
1.የእህል ዘር
2.የዕፅዋትና ቅጠላ ቅጠል ዘር
3.የአገዳ ዘር
5.ማዕድናት
6.እንስሳት
7.ከእንስሳት ተዋጽዖ የሚገኙ ናቸው።
🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢
*የተፈጥሮ ስርዓቶች 7 ናቸው።እነርሱም፦
1.የተፈጥሮ አለመዛነፍ
2.የተፈጥሮ ተቃርኖ
3.የተፈጥሮ መርጋት
4.የተፈጥሮ ረቂቂነት
5.የተፈጥሮ ኃይል
6.የተፈጥሮ መታደስ
7.የተፈጥሮ ምስጢራዊነት ናቸው።
🚢🚢🚢🚢🚢🚢
*የተፈጥሮ አለመዛነፍ ሲባል ለምሳሌ ግራቪቲ አይዛነፍም።አውሮፕላን የተሰራው ግራቪቲን በመተማመን መሆኑ ይታወቃል።ግራቪቲ ከተዛነፈ አለም ትናጋለች።የተፈጥሮ ተቃርኖ ማለት ብርሃን/ጨለማ፣መወለድ/ሞት፣ሰማይ/መሬት/፣ወንድ/ሴት ማለት ሲሆን ኃይል አለው።ለምሳሌ መኪናችንን የምናስነሰው - እና + ቻርጅ ኃይል ሰጥተን ነው።ሰው የሁለት ተቃርኖች ውጤት ነው።ከተቃርኖ ኃይል ይወለዳል።
🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢
*በኢትዮጵያ 7 ዕጽዋት አሉ።
1.ዕፀ አበው
2.ዕፀ በትረ ዳዊት
3.ዕፀ ሙሴ
4.ዕፀ ህይወት
5.ዕፀ በለስ
6.ዕፀ ሳቤቅ
7.ዕፀ ሀረገ ወይን ናቸው።
🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢
*እነዚህ እጾች ኢትዮጵያ ብቻ ይገኛሉ። በሽታ ያድናሉ፣የተፈጥሮ አደጋን ይከላከላሉ፣አይምሮን ያበለጽጋሉ፣ዕድሜ ይቀጥላሉ፣ኃይል ይሰጣሉ።ህይወት ቀጣይ ዕጿ ልብ ቅርፅ አላት።በአመት አንድ ጊዜ ትበቅላለች።አረምን ለምሳሌ ዕንቦጭን የሚያጠፉ ዕጽዋቶች አሉ።
🚢🚢🚢🚢
#
1535
19:22
29.06.2023
close
New items
Selected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий